album cover
Lebo
3,129
World
Lebo was released on January 1, 2002 by AIT Records, Inc. as a part of the album Teddy
album cover
AlbumTeddy
Release DateJanuary 1, 2002
LabelAIT Records, Inc.
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM173

Credits

COMPOSITION & LYRICS
Theodros Kassahun
Theodros Kassahun
Songwriter

Lyrics

የደመቀው ጀንበር: ይጠቁራል በክረምት
እድሜም በወቅት ያልቃል: መውደድ በወረት
እውነተኛ አፍቃሪ: ማህተቡ ለፅድቅ
ሲኖር አብሮ በልቶ: ሲቸገሩ አይርቅ
የበደል አበባ: ያበቃላት ለቅሶ
ፍቅር ነኝ ትላለች: ደግሞ በርሷም ብሶ
ቢወሻሽ ነው እንጂ: አንዱም ላይጎዳ
ምን አሸዋወደው: አራዳ ላራዳ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
ሲርቋት ተከታይ: ሲላመዷት ባዳ
አትዘልቅም ካንድ ቤት: ሁለት ቢላ ለምዳ
አመሏ አይታወቅ: ፌዝ ያገነናት
እሳት ሲሏ ውሃ: ማር ሲላት እሬት
እንደሰማይ ጀንበር: ሁሌ እየደመቀ
ተመልሶ አይወጣም: እድሜም ከጠለቀ
ዘመን እያባራ: ሁሌ አይኖር ስቆ
ውበትም ይመሻል: ጊዜው ጠብቆ
ጀንበር ሲጠልቅ ሲሸሽ: ሳቅ ሲተካው ለቅሶ
ያ ያማረው ወራት: አይገኝ መልሶ
መወደዷን አውቃ: መልኳ ስላማረ
እኮራለሁ ብላ: ተረስታ ነበረ
በይ እኮ!
የደመቀው ጀንበር: ይጠቁራል በክረምት
እድሜም በወቅት ያልቃል: መውደድ በወረት
እውነተኛ አፍቃሪ: ማህተቡ ለፅድቅ
ሲኖር አብሮ በልቶ: ሲቸገሩ አይርቅ
የበደል አበባ: ያበቃላት ለቅሶ
ፍቅር ነኝ ትላለች: ደግሞ በርሷም ብሶ
ቢወሻሽ ነው እንጂ: አንዱም ላይጎዳ
ምን አሸዋወደው: አራዳ ላራዳ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መሄድ መሄድ ያለ: ውሎ አዳሩ ደጅ
እንኳንስ ለወዳጅ: ለራሱም አይበጅ
ያንጀት ወዳጅ መስሎ: ትልቅ ጉድጓድ ምሶ
ንጉሥም ለብልሃት: ያበላል ደግሶ
መስቀል ዘ ሰላጢን: ከመፅሐፍ ጠቅሳ
እመነኝ አለችኝ: ልትቀብረኝ ምሳ
ተምራ ተክና: ላሳር ለኩነኔ
ደቁና ስትመጣ: ቄስ ሆንኩባት እኔ
ጀንበር ሲቀር ሲሸሽ: ሳቅ ሲተካው ለቅሶ
ያ ያማረው ወራት: አይገኝ መልሶ
መወደዷን አውቃ: መልኳ ስላማረ
እኮራለሁ ብላ: ተረስታ ነበረ
እንደሰማይ ጀንበር: ሁሌ እየደመቀ
ተመልሶ አይወጣም: እድሜም ከጠለቀ
ዘመን እያባራ: ሁሌ አይኖር ስቆ
ውበትም ይመሻል: ወራቱን ጠብቆ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
መስረቅ ተቃርቦ: ተይ ይቅር ሌቦ
Written by: Theodros Kassahun
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...