Music Video
Music Video
Credits
PERFORMING ARTISTS
Kuku Sebsebe
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Elias Melka
Songwriter
Lyrics
በጉንጮቼ ወለል ሲፈስ የሚታየኝ
እባክህ አስረዳኝ ዝናብ ነው እንባ ነው
በየመንገዱ ላይ በጋራ በወንዙ
የሰማዩ ዝናብ ይዘንባል በብዙ
ለተመለከተው ይገርማል ይደንቃል
ካዓይኖቼ የሚፈሰው መች አባርቶ ያውቃል
ከአንጀቴ ከሆነ እንባዬ የሚፈሰው
ምክንያቱ አንተነህ አላውቅም ሌላ ሰው
እኔ እወድሃለሁ ፍቅሬ አስብሃለሁ
ህይወቴ በሙሉ ያንተ ይሁን ብያለው
ህይወቴ በሙሉ ያንተ ይሁን ብያለው
እኔ እወድሃለሁ ፍቅሬ አስብሃለሁ
ህይወቴ በሙሉ ያንተ ይሁን ብያለው
ህይወቴ በሙሉ ያንተ ይሁን ብያለው
የሰማዩ ዝናብ ከዳመናው መጣ
ከዐይኔ የሚመነጨው እረ ከየት መጣ
ተመራምሬያለው እኔ ግን በሀሳቤ
እንባዬ አየመጣ ነው እኮ ከልቤ
ክረምት አልፎ በጋ ሁሌ አይቀርም ሲባል
የኔ እንባ አላባራም ገና ነው ይዘንባል
ከአንጀቴ ከሆነ እንባዬ የሚፈሰው
ምክንያቱ አንተነህ አላውቅም ሌላ ሰው
እኔ እወድሃለሁ ፍቅሬ አስብሃለሁ
ህይወቴ በሙሉ ያንተ ይሁን ብያለው
ህይወቴ በሙሉ ያንተ ይሁን ብያለው
እኔ እወድሃለሁ ፍቅሬ አስብሃለሁ
ህይወቴ በሙሉ ያንተ ይሁን ብያለው
ህይወቴ በሙሉ ያንተ ይሁን ብያለው
Written by: Elias Melka


