Lyrics

እስኪ ዶሴዉ ይዉጣ የምጠየቅበት ወንጀሌን ሳላዉቀዉ እኔ አልቀጣበት እኔ አልቀጣበት በማላዉቀዉ ጉዳይ ከመሰላት ዉላ የተከሰስኩ እኔ የደፈራት ሌላ የደፈራት ሌላ እስኪ ዶሲዉ ይዉጣ የምጠየቅበት ወንጀሌን ሳላዉቀዉ እኔ አልቀጣበት እኔ አልቀጣበት በማላዉቀዉ ጉዳይ ከመሰላት ዉላ የተከሰስኩ እኔ የደፈራት ሌላ የደፈራት ሌላ የሞላ ማድጋ አያዉቀዉም ሽንጧን እኔም አልክደዉም ሙሉ መቆየቷን ስወድሽ እንደሆን ሁሉም ስላወቀዉ በግምት ብቻ ነዉ የምጠረጠረዉ እይ አይ አሃሃሃይ ልጥላ ወይ ልዉደድሽ ደግም አልዋልሽልኝ ወዳጄ እንዳትባይ በጎ አላሰብሽልኝ የድብቅ የድብቅ ድንገት ባደረግሽዉ አስወነጀልሽኝ ወይ በኔ ላይ ላከክሽዉ አምባሩን ያጌጠበት ሌላ ተከሳሽ አምሮት ያጣ ገላ አምባሩን ያጌጠበት ሌላ ተከሳሽ አምሮት ያጣ ገላ ምስክር አልጠራ ወንጀለኛ እንዳልሆን ሆኗል ያሉት ነገር ሰዉ እያየን አይሆን ጅምሩን ይጨርስ ቢሉም ቢፈርዱብኝ እዳዉን አምኖ እንጂ ወዶ አገባ አይሉኝ እይ አይ አሃሃሃይ እንዳጎደልሽብኝ ሙሉ ሙሉ ስልሽ እኔ አልነበርኩም ወይ ጠያቂም ወቃሽሽ ለአንቺ ገላ መዉደቅ ሳለዉ አስታማሚዉ የት ዉለሽ ማን ቀርቦሽ አቦሉን ካደምሽዉ አፍቅሮሽ ስንቱን ባዬ ጎኔ እንዴት ክስ መጥሪያ አመጣሽ ለኔ አፍቅሮሽ ስንቱን ባዬ ጎኔ እንዴት ክስ መጥሪያ አመጣሽ ለኔ እስኪ ዶሴዉ ይዉጣ የምጠየቅበት ወንጀሌን ሳላዉቀዉ እኔ አልቀጣበት እኔ አልቀጣበት በማላዉቀዉ ጉዳይ ከመሰላት ዉላ የተከሰስኩ እኔ የደፈራት ሌላ የደፈራት ሌላ እኔን የሚያሳማኝ ያስጠየቀኝ ነገር ድፍን የሀገሩን ወንድ አይቀር ከማስጠርጠር ምነዉ ጉድ አመጣ ለአንቺ መታመኔ ሲሞላ ከሌላዉ ሲጎልብሽ ከእኔ እይ አይ አሃሃሃይ ያረግሽኝን ነገር ባምንም አቅልዬልሽ ለኋላስ ኑሯችን እንዴት ነዉ የማምንሽ እኔ ባላረኩት ሸምጠሸ ከዋሸሽ ልቤ እንዴት ይታረቅ ከጅምሩ ጎለሸ አጋጥሞት ሳለ የሰረቀዉ ጭምቱን ጉዳዩ አስጠየቀዉ አጋጥሞት ሳለ የሰረቀዉ ጭምቱን ጉዳዩ አስጠየቀዉ አጋጥሞት ሳለ የሰረቀዉ ጭምቱን ጉዳዩ አስጠየቀዉ
Writer(s): Elias Woldemariam, Tsegaye Deboch Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out