album cover
Yaferarsegnal
album cover
Yaferarsegnal was released on June 9, 2026 by Sonic ሶኒክ as a part of the album Mushraye (ሙሽራዬ)
June 9, 2026
LabelSonic ሶኒክ
LanguageEnglish
BPM99
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy

Music Video

Music Video

Lyrics

ያፈራርሰኛል
ጨለማው ሲነግስ ክፍሉ ሲቀዘቅዝ
መንፈሴ ይባንናል
ትዝታሽን ሲጠጣ እንደ መርዝ
የከንፈርሽ ጣዕም የቆዳሽ ሽታ
በደም ስሬ ፈሰሰ
ልቤን አሳጣው ፋታ
አውቃለሁ ስህተት ነው መንገዱ አያምርም
ግን ካንቺ መራቅስ ለኔ ሞት አይደለምን?
እንደ ጭስ ተኖ እንደሚጠፋ ተስፋ
በናፍቆትሽ ባህር ነፍሴ ልትሰምጥ ነው
ልትጠፋ
ብረሳሽ እላለሁ ስምሽን ሳልጠራ
ግን ልቤ ይከዳኛል ካንቺ ጋር ሳወራ
ትዝታሽ ገደለኝ ሳስብሽ በማታ
መውጫው ጠፋኝና ልቤ ባንቺ ተረታ
እንደ Chemical በደሜ ተዘዋወርሽ
መውጫ የሌለው ሱስ ነፍሴን የወረስሽ
ለመሄድ ብሞክር እግሬ ይዝላል
ፍቅርሽ መርዝ ሆኖ ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
ያፈራርሰኛል
ኦ...
Noo... ኦ...
በቃኝ እላለሁ በሩን ዘግቼ ስወጣ
የመኪናዬ ሽታ ያንቺን ትዝታ ሲያመጣ
እንደገና ተመልሼ ደጅሽ ላይ እቆማለሁ
የገዛ እራሴን ቃል መልሼ እበላለሁ
የደም ዝውውሬን ቀይረሽዋል
የአእምሮዬን ሰላም ሰርቀሽዋል
መርዝሽ ይጣፍጣል ገዳይ ነው ግን
በፍቅርሽ ታውሬ ጠፋሁኝ ሆኜ ካንቺው ጎን
ብረሳሽ እላለሁ ስምሽን ሳልጠራ
ግን ልቤ ይከዳኛል ካንቺ ጋር ሳወራ
ትዝታሽ ገደለኝ ሳስብሽ በማታ
መውጫው ጠፋኝና ልቤ ባንቺ ተረታ
እንደ Chemical በደሜ ተዘዋወርሽ
መውጫ የሌለው ሱስ ነፍሴን የወረስሽ
ለመሄድ ብሞክር እግሬ ይዝላል
ፍቅርሽ መርዝ ሆኖ ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
ተዋህደናል (እንደ Chemical)
ልላቀቅሽ አልችልም (እንደ Chemical)
ሱሴ ነሽ በቃ
ያፈራርሰኛል (እንደ Chemical)
ኦ... (እንደ Chemical)
ኦ... ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
(ኦ...)
ያፈራርሰኛል
(ኦ... )
(ኦ... )
ያፈራርሰኛል
ያፈራርሰኛል
ያፈራርሰኛል
Written by: Alpha Tadesse
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...