Credits

PERFORMING ARTISTS
Neway Debebe
Neway Debebe
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Neway Debebe
Neway Debebe
Songwriter

Lyrics

ያለፍኩ እንደሆን በአንቺ መንደር (በፍቅር)
ቅር ቅር ይለኛል በዚያዉ እደር (ወይ ችግር)
ከቤትሽ ደጃፍ ቆመሽ በእግርሽ (ሲቃኝሽ)
እያስተዋልሽዉ አይኔን በአይንሽ (ሲወድሽ)
ሂድም እንድ ነዉ ግባ አላልሽኝ
ወይ አጋጣሚ ጉድ ሰራሽኝ
የኔዉ ጉዳይ ነዉ ምን አደርጋለሁ
ቀን ያካክሳል እችለዋለሁ
ሂድም እንድ ነዉ ግባ አላልሽኝ
ወይ አጋጣሚ ጉድ ሰራሽኝ
የኔዉ ጉዳይ ነዉ ምን አደርጋለሁ
ቀን ያካክሳል እችለዋለሁ
የደጅሽን መንገድ በእሾክ አሳጥሪዉ
ቋጥኝ አስፈልፍለሽ በከባ አስከልክይዉ
ኳትኖስ መች ሆነለት ልምምጥ ተረፈዉ
የፍቅርሽ ነበልባል ወላፈን ገረፈዉ
የፍቅርሽ ነበልባል ወላፈን ገረፈዉ
ሸግዬ መቼም አይሆንለት ሸግዬ መች በዋል ፈሰሰ ሸግዬ
ፍቅርሽ ያጠቃዉን ሸግዬ ወዳጁን ማወደስ ሸግዬ
በምን ቃላት ልግለፅ ሸግዬ በምን ቋንቋ ላዉራ ሸግዬ
ህመሜ ተሰምቶት ሸግዬ ልብሽ እንዲራራ ሸግዬ
እንዲያዉ ሸጌ ሸጌ ሸግዬ አረ ሸጌ ሸጌ ሸግዬ
እንዲያዉ ሸጌ ሸጌ ሸግዬ አረ ሸጌ ሸጌ
ያለፍኩ እንደሆን በአንቺ መንደር (በፍቅር)
ቅር ቅር ይለኛል በዚያዉ እደር (ወይ ችግር)
ከቤትሽ ደጃፍ ቆመሽ በእግርሽ (ሲቃኝሽ)
እያስተዋልሽዉ አይኔን በአይንሽ (ሲወድሽ)
ሂድም እንድ ነዉ ግባ አላልሽኝ
ወይ አጋጣሚ ጉድ ሰራሽኝ
የኔዉ ጉዳይ ነዉ ምን አደርጋለሁ
ቀን ያካክሳል እችለዋለሁ
ሂድም እንድ ነዉ ግባ አላልሽኝ
ወይ አጋጣሚ ጉድ ሰራሽኝ
የኔዉ ጉዳይ ነዉ ምን አደርጋለሁ
ቀን ያካክሳል እችለዋለሁ
ከመኳተን አልዳንኩ እንዲገባሽ ብዬ
ልቤ ካንቺዉ ዘምቷል እርጅኝ አበባዬ
ፍስሀሽ የከዳቸዉ ጉንጮቼ ወረዙ
በእምባ ለመታጠብ ምክንያት አበዙ
በእምባ ለመታጠብ ምክንያት አበዙ
ሸግዬ አንቺን አሸንፎ ሸግዬ ልብ አይቀዳጅም
ሸግዬ ልቤ በፍቅር ያምናል ሸግዬ ታዉቂዋሽ አንቺም
ሸግዬ በምን ቃላት ልግለፅ ሸግዬ በምን ቋንቋ ላዉራ
ሸግዬ ህመሜ ተሰምቶት ልብሽ እንዲራራ ሸግዬ
እዲያዉ ሸጌ ሸጌ ሸግዬ
አረ ሸጌ ሸጌ ሸግዬ እዲያዉ ሸጌ ሸጌ ሸግዬ አረ ሸጌ ሸጌ
Written by: Neway Debebe
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...