album cover
Bati
639
World
Bati adlı parça albümünün bir parçası olarak Triple Earth tarafından 1 Ocak 1990 tarihinde yayınlandıKabu
album cover
AlbümKabu
Çıkış Tarihi1 Ocak 1990
FirmaTriple Earth
Melodiklik
Akustiklik
Valence
Dans Edilebilirlik
Enerji
BPM59

Krediler

PERFORMING ARTISTS
Aster Aweke
Aster Aweke
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Trad. arr: Aster Aweke
Trad. arr: Aster Aweke
Songwriter

Şarkı sözleri

ጊዜው ይርዘም እንጂ መች እረሳሀለው
በሆነው ባልሆነው እናፍቅሀለው
በል ይግረምህ እና ዛሬም ወድሀለው
አንጀቴን አስሬ ይኸው እኖራለው
ርቄ ሄጃለው ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን ያንተ ሚስጥር
ተማምነው ተዋደው አብረው የኖሩት
ሲለዩት ይፋጃል እንደ እግር እሳት
እንደ እግር እሳት
በልቤ ወድጄ በአፌ የማቀብጥህ
ትቼ የማልተውህ እኔው ነኝ ወዳጅህ
አይቻልም እና የአንዳንድ ሰው ናፍቆት
መውደድን በወጉ ፍቅር ያስተማሩት
ርቄ ሄጃለው ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን ያንተ ሚስጥር
የልቤ ምሰሶ ዘንጉ ተሰበረ
የማይመነጠር ምሽግ የነበረ
ምሽግ የነበረ
በፅኑ ትዝታ በራቀው መንገዴ
እስቲ ላሰላስልህ ደግሞ እንደ ልማዴ
ይኸው ልቤ ጥሎኝ ተነስቶ ሲሄድ
ባንተ መወስወሱን አድርጎ ልማድ
አድርጎ ልማድ
Written by: Trad. arr: Aster Aweke
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...