album cover
Kiber
24
Christian & Gospel
Kiber adlı parça albümünün bir parçası olarak ሮdb Records tarafından 1 Nisan 2022 tarihinde yayınlandıYehagere Lij
album cover
Çıkış Tarihi1 Nisan 2022
Firmaሮdb Records
Melodiklik
Akustiklik
Valence
Dans Edilebilirlik
Enerji
BPM92

Krediler

PERFORMING ARTISTS
Ebba Daniel Deressa
Ebba Daniel Deressa
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Ebba Daniel Deressa
Ebba Daniel Deressa
Songwriter

Şarkı sözleri

የምስጋና ነዶ ታቅፈናል
በገናን ይዘናል ደስ ብሎናል
ከነበርንበት ከዛ ጨለማ
ብርሃን ስላየን ወንጌል ስንሰማ
ጨመርን አምልኳችንን
ጨመርን ምስጋናችንን
ቀን ከሌት ብንዘምረው
ማዳንህ እጅግ ብዙ ነው
ጨመርን አምልኳችንን
ጨመርን ምስጋናችንን
ቀን ከሌት ብንዘምረው
ኢየሱስ ፍቅርህ ብዙ ነው
ከፃድቃን ጉባኤ በጽዮን ተራራ
ከቅዱሳኑ ጋራ ስማችን እንዲጠራ
አፍስሰህልናል ኢየሱስ ውድ ደምህን
ከብረናልና በአንተ ክበር እንላለን
ክበር ክበር ክበር
እናክብርህ እንደገና
ለአንተ ይብዛልህ ምስጋና
ንገስ ንገስ ንገስ
እናንግስህ እንደገና
ለአንተ ይብዛልህ ምስጋና
የምስጋና ነዶ ታቅፈናል
በገናን ይዘናል ደስ ብሎናል
ከነበርንበት ከዛ ጨለማ
ብርሃን ስላየን ወንጌል ስንሰማ
ጨመርን አምልኳችንን
ጨመርን ምስጋናችንን
ቀን ከሌት ብንዘምረው
ማዳንህ እጅግ ብዙ ነው
ጨመርን አምልኳችንን
ጨመርን ምስጋናችንን
ቀን ከሌት ብንዘምረው
ኢየሱስ ፍቅርህ ብዙ ነው
የማይገባንን ፀጋ ላለበስከን
የአባትህን መንግስት በእምነት ላወረስከን
ከነገድ ከቋንቋ ዋጅተህ ካደረከን ደቀመዝሙር
ገና እንጨምራለን በክብር ላይ ክብር
ክበር ክበር ክበር
እናክብርህ እንደገና
ለአንተ ይብዛልህ ምስጋና
ንገስ ንገስ ንገስ
እናንግስህ እንደገና
ለአንተ ይብዛልህ ምስጋና
Written by: Ebba Daniel Deressa
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...