album cover
Eyulign
album cover
Eyulign adlı parça {albumName} albümünün bir parçası olarak Aster Abebe tarafından 4 Ekim 2024 tarihinde yayınlandıHallelujah
4 Ekim 2024
FirmaAster Abebe
BPM138
Melodiklik
Akustiklik
Valence
Dans Edilebilirlik
Enerji

Müzik Videosu

Müzik Videosu

Şarkı sözleri

ኢየሱስ (12)
ላውራው ልዘምረው
ልናገር ልተርከው
ልጥራው ልደጋግመው
ልመርኮዝ ልደገፈው
ስሙ ከፊደል ያለፈ ነው
ስሙ ከአንድ ቃል ያለፈ ነው
ስሙ ከስሞች ያለፈ ነው
ስሙ ከምለው ያለፈ ነው
ስምህን ስጠራው ጥሜ ይረካልኛል
ስምህን ስጠራው ከረሃቤ እጠግባለሁኝ
ስምህን ስጠራው ጥሜ ይረካልኛል
ስምህን ስጠራው ከረሃቤ እጠግባለሁኝ
ለዚህ ነው ሲነጋ ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው በቀትር ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው ሲመሽም ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው በሌሊት ኢየሱስ የምለው
በምን አጎደልከኝ መች ጠናሁ የሰው ደጅ
ከጫፍ ጫፍ ሙላቴ የምትደላ የምትመች
ሰው እንኳን የሚያልፈውን ይሄ አለኝ ይላል
አንድ ሁለት ሶስት ብሎ ለሚያይ ያስቆጥራል
የማታልፍ የማታልቅ የማትደክም ትምክህቴ
የማልቀይርህ መዝሙር እስካለሁ በህይወቴ
ለልጅ ልጅ ትምህርት ርስትም ያለኸኝ
ለሚያዩኝ ሁሉ እዩልኝ የሚያስብለኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ምህረቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ምህረቱን እዩልኝ
ከማይደረስበት ከቅድስናው ጥግ በሞቱ አድርሶኝ
ፀድቀሻል አለኝ እዩልኝ
ካለሁበት ሸለቆ ህያው ቃሉን ልኮ ዳግም ሰው አድርጎኝ
አንቺ ብርቱ አለኝ እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ምህረቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ምህረቱን እዩልኝ
Written by: Aster Abebe
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...