album cover
Ayzenegash Libe
album cover
Ayzenegash Libe adlı parça {albumName} albümünün bir parçası olarak Teddy Afro tarafından 1 Nisan 2012 tarihinde yayınlandıTikur Sew
AlbümTikur Sew
1 Nisan 2012
FirmaTeddy Afro
BPM117
Melodiklik
Akustiklik
Valence
Dans Edilebilirlik
Enerji

Şarkı sözleri

የብርሃን ሰልፍ ነው ያነገተ ፍቅር ሰላም
ጤና ለአዳም
እንኳን ሰው እንስሳም የፍቅር ነው ሰራዊቱ
ዱር አራዊቱ
ምን አስተከዘህ ከሃዘን ዋሻው
የኔ ሆድ ባሻው
ባሻው ይደሰት ልብህ ከቶም እንዳይከፋው
አዝነህ ላትገፋው
ቢከፋም ቢለማም ያለም ኑሮህ ምን ባይቀና
ሁን አንተ ጤና
ቸር አስብበት በሰጠህ እድሜ
አይዞህ ወንድሜ
ድንገት ቢከፋህ ባይቀናህ ኑሮ
በዚህች ዓለም
ጊዜ የማይፈታው ምንም የለም
ጊዜም አሁን ነው ትናንት ሆኖ ቀሪ
የነገው ቀን ሰሪ
ዓመት ያህላል ቀን እየዞረ
ዛሬም እራሱ ነገ ነበረ
የጊዜ ሚዛን አይላወስም
ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም
ሳዝን አልውልም ሳላውቅ ማደሬን
የኔ ነው በቃ አልሰጥም ዛሬን
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
ባሻው ይደሰት ልብሽ ከቶም እንዳይከፋው
አዝኖ ላይገፋው
ቢከፋም ቢለማም
የዓለም ኑሮሽ ምን ባይቀና
ሰርክ አንቺ ደህና
ፍቅርን ሳይበት ኑሪና በዓለም
አንቺ የእናት ቀለም
ቀኑ ቢመሻሽ
ብለሽ አትስጊ ፋኖስ የለም
ፀሃይ ነሽና ለዚች ዓለም
ዛሬን አብሪበት ለኩሺና ተስፋ
ነገም እንዳይጠፋ
ዓመት ያህላል ቀን እየዞረ
ዛሬም እራሱ ነገ ነበረ
የጊዜ ሚዛን አይላወስም
ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም
ሳዝን አልውልም ሳላውቅ ማደሬን
የኔ ነው በቃ አልሰጥም ዛሬን
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
አይዞህ ልቤ አይዞህ
Written by: Teddy Afro
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...