Credits
PERFORMING ARTISTS
Hanna Tekle
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Hanna Tekle Sarhe
Songwriter
Lyrics
ባነበብን ቁጥር ባወቅነው
የማንለምደው ቃልህን
በገባን ቁጥር ባወቅነው
ምንፈልገው ቃልህን ነው
ዛሬም እንድትልልን ሳይሆን
ልትል ያሰብከው ያግኘን
ያለመከልከል ተናግረህ
ያለገደብ ሥራብን
መንፈስህ ይግዛን
ይስፈንብን በሙላት
የልብህ አሳብ ያጥምደን
የሚያቆመን ያ ነው በጽናት
እናድጋለን እንጂ ሰርክ ወደ አንተ
ልናድግ አይቻለንም በአንተ ላይ
ከፍለን ባወቅንህ ቁጥር
ዝግ እንበል እንይ ወደላይ
ምን ብናውቅ ጥበብ ቢጠጋን
ሲመስለን ያወቅን የበቃን
አናውቅም ባወቅንህ ቁጥር
ደቀመዝሙር ነን ሁሌ በአንተ ሥር
ተማሪዎች ነን ሁሌ ልጆችህ
መቼም በማንጨርሰው ትምህርትህ
ከፍለን ባወቅነው ጥቂት
ትሑት አድረገን ባንተ ፊት
ታማኝ አድረገን ለቃልህ
አብቃን ለውድ አሳብህ
መስታወት በሆነው ቃልህ
አንቃን በውድ መንገድህ
ተናገር ኢየሱስ
ተናገር በኃይል
እንሰማሃለን
ተናገር መንፈስ ቅዱስ
ተናገር በሙላት
እንሰማሀለን
ተናገር እንሰማሀለን
ተናገር እንሰማሀለን
ባነበብን ቁጥር ባወቅነው
የማንለምደው ቃልህን
በገባን ቁጥር ባወቅነው
ምንፈልገው ቃልህን ነው
Written by: Hanna Tekle Sarhe

