Lyrics

ልቤ ብዙ ብዙ ይመኛል የአንተን ጥሎ ወዲያ ይሮጣል አሳልፈህ አትስጠኝ ለራሴ ባንተ ልኑር አልቁም በራሴ ልቤ ብዙ ብዙ ይመኛል የአንተን ጥሎ ወዲያ ይሮጣል አሳልፈህ አትስጠኝ ለራሴ ደርሶ አሳቢ ስሆን ለራሴ እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ ፍቃድህ በልቤ ላይ ትሁን ትሰረኝ በራሴም አልሁን ቀድመኸኝ ከወጣህ ከፊቴ አልፈራም ብርቱ ነኝ አባቴ ጥላህ ስር በምቾት አድራለው ዘመኔን ባንተ ስር ካረከው ፍቃድህ በልቤ ላይ ትሁን ትሰረኝ በራሴም አልሁን ቀድመኸኝ ከወጣህ ከፊቴ አልፈራም ብርቱ ነኝ አባቴ ጥላህ ስር በምቾት አድራለው ዘመኔን ባንተ ስር ካረከው የተከፈተ በር ሁሉ ካንተ አይደለም ነግ ሊያጎድለኝ እንጂ ለመልካም አይደለም ተደባልቆ የገባን ስኬቴ አውጣልኝ ከቤቴ ከቤቴ ሁሉ የሞላበት የሀሰት ገነት ምን ሊበጅ ያላንተ አንተ የለህበት ይሻል የለ ያንተው በረሃ ሳላይ እህል ውሃ እህል ውሃ ዝጋብኝ የስኬትን መንገድ ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ የነገን እዳ እፈራለሁ ሰግቼ ለምን እኖራለሁ ይቅርብኝ የምቾቴ መንገድ ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ የነገን ቁጣ እፈራለሁ ሰግቼ ለምን እኖራለሁ እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ ያንተን ውድ ጊዜ መጠበቅ አቅቶኝ የልብህን ሀሳብ መታገስ ተስኖኝ የፈጠንኩ ሲመስለኝ ዘግይቼ እንዳልገኝ ካየኸው ወርጄ የእንጀራ ጩኸቴ ፅኑ ልመናዬ በሞላልኝ ማግስት እንዳይሆን ገዳዬ አንተ ያልከው ይሁን በህይወቴ እኔ አልቅደም ቅደመኝ አባቴ ዝጋብኝ የስኬትን መንገድ ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ የነገን እዳ እፈራለሁ ሰግቼ ለምን እኖራለሁ ይቅርብኝ የምቾቴ መንገድ ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ የነገን ቁጣ እፈራለሁ ሰግቼ ለምን እኖራለሁ እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ እንደ ልብህ ልሁን እንደ ልብህ እንደ ሃሳብህ ልኑር እንደ ፍቃድህ
Writer(s): Samuel Alemu, Hanna Tekle Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out