音乐视频

音乐视频

制作

出演艺人
Abdu Kiar
Abdu Kiar
表演者
作曲和作词
Abdu Kiar Kahssay
Abdu Kiar Kahssay
词曲作者

歌词

የቱ ውበት ነው እንዳንቺ የተዋጣለት
የቱ አመል ነው እንከን የማይገኝለት
ልብን ወስዶ መንፈስን የሚገዛ
የሚያሸንፍ ቀን በቀን የሚበዛ
ይሄ ሁሉ መባረክና ማማር
ከየት ነው ምንጩ ንገሪኝ እስቲ የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
ውበት ቁንጅናሽን በቃል ለማስረዳት
የቋንቋ እውቀት ያለው ያስፈልጋል ረዳት
ቃላት ላይ ፊደል ላይ ስልጣን የሌለው ሰው
አይችልም አይችልም ውበትሽን ሊገልጸው
ውበት ቁንጅናሽን በቃል ለማስረዳት
የቋንቋ እውቀት ያለው ያስፈልጋል ረዳት
ቃላት ላይ ፊደል ላይ ስልጣን የሌለው ሰው
አይችልም አይችልም ውበትሽን ሊገልጸው
ቆንጆ ናት መቼ ይገልጽሻል
ቁም ነገር አስቀርቶብሻል
ጥሩ ናት መቼ ይገልጽሻል
ውበትን ይደብቅብሻል
የኔ ማር ቃል እስካገኝ ድረስ
የኔ ማር የሚሄድ ካንቺ ጋር
የኔ ማር ዝም ብዬ ልውደድሽ
የኔ ማር እያልኩሽ የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
የቱ ውበት ነው እንዳንቺ የተዋጣለት
የቱ አመል ነው እንከን የማይገኝለት
ልብን ወስዶ መንፈስን የሚገዛ
የሚያሸንፍ ቀን በቀን የሚበዛ
ይሄ ሁሉ መባረክ እና ማማር
ከየት ነው ምንጩ ንገሪኝ እስቲ የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
የማማርሽ ዝና ተዳርሶልሽ ባለም
ስታምር ስታምር የማይልሽ የለም
የውበት መለኪያው ሳይለካ ኖሮ
ውበት ማለት አንቺ ሆነሻል ዘንድሮ
የማማርሽ ዝና ተዳርሶልሽ ባለም
ስታምር ስታምር የማይልሽ የለም
የውበት መለኪያው ራሱ ተለክቶ
መለካቱን ትቷል ባንቺ ተተክቶ
ቆንጆ ናት መቼ ይገልጽሻል
ቁም ነገር አስቀርቶብሻል
ጥሩ ናት መቼ ይገልጽሻል
ውበትን ይደብቅብሻል
የኔ ማር ቃል እስካገኝ ድረስ
የኔ ማር የሚሄድ ካንቺ ጋር
የኔ ማር ዝም ብዬ ልውደድሽ
የኔ ማር እያልኩሽ የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
የኔ ማር የኔ ማር
Written by: Abdu Kiar Kahssay
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...