制作
出演艺人
Girma Tefera Kassa
表演者
作曲和作词
Meselle Getahun
词曲作者
RR
词曲作者
歌词
ልክ እንዳየሁሽ ልቤ እርብሽ አለብኝ
ለካ እንዲህ ውብ ነሽ እኔስ ማመን ተሳነኝ
ልክ እንደ አዲስ ሰው ሆኜ ዛሬ ብመኝሽ
ሲያምረኝ ይቅር እንጂ መቼም ከሰው አልቀማሽ
ድሮም በጅ የያዙት ከምን ይቆጠራል
ደግሞ በሠው ሲያዩት ተመልሶ ያምራል
ፍቅር አይሉት ቅናት ምን ይሆን ነገሩ
ከሰው ጋራ ሳይሽ ልቤ መሸበሩ
ልክ እንዳየሁሽ ልቤ እርብሽ አለብኝ
ለካ እንዲህ ውብ ነሽ እኔስ ማመን ተሳነኝ
ልክ እንደ አዲስ ሰው ሆኜ ዛሬ ብመኝሽ
ሲያምረኝ ይቅር እንጂ መቼም ከሰው አልቀማሽ
አቤት እንዴት ይገርማል ቆንጅተሻል አምረሻል
ምን ዋጋ አለው ይገርማል አንዴ ከጄ ወጥተሸል
ዛሬ ሳይሽ ይገርማል እንደገና ይገርማል
አማለልሽኝ ይገርማል አማርሽና ይገርማል
ለካ እንዲህ ውብ ነሽ እኔስ ማመን ተሳነኝ
ልክ እንደ አዲስ ሰው ሆኜ ዛሬ ብመኝሽ
ሲያምረኝ ይቅር እንጂ መቼም ከሰው አልቀማሽ
አብረሽኝ እያለሽ ደስተኛ መሆኔን
ምን ነበር እንዳላይ የጋረደው አይኔን
ያን ጊዜ ቁንጅናሽ ላይኔ እንኳን ሳይሞላ
ዛሬ አመረሽ ታየሽኝ ሳገኝሽ ከሌላ
ልክ እንዳየሁሽ ልቤ እርብሽ አለብኝ
ለካ እንዲህ ውብ ነሽ እኔስ ማመን ተሳነኝ
ልክ እንደ አዲስ ሰው ሆኜ ዛሬ ብመኝሽ
ሲያምረኝ ይቅር እንጂ መቼም ከሰው አልቀማሽ
አቤት እንዴት ይገርማል ቆንጅተሻል አምረሻል
ምን ዋጋ አለው ይገርማል አንዴ ከጄ ወጥተሸል
ዛሬ ሳይሽ ይገርማል እንደገና ይገርማል
አማለልሽኝ ይገርማል አማርሽና ይገርማል
አቤት እንዴት ይገርማል ቆንጅተሻል አምረሻል
ምን ዋጋ አለው ይገርማል አንዴ ከጄ ወጥተሸል
ዛሬ ሳይሽ ይገርማል እንደገና ይገርማል
አማለልሽኝ ይገርማል አማርሽና ይገርማል
Written by: Meselle Getahun, RR