歌词
የምለምንህ ወድጄህ ወድጄህ አፍቅሬህ እንጂ
አትሂድ የምልህ ወድጄህ ወድጄህ አፍቅሬህ እንጂ
አንተን ካጣው መኖር የማልችል
ነብሴ በእጅህ ያለች ይመስል
ምነው ይሄን ያህል
ምነው ይሄን ያህል
ምነው ይሄን ያህል እንዴ
ምነው ይሄን ያህል
ልቤ እንደሚያፈቅርህ አውቃለው አልክድም
ባንተላይ ጨክኖ አንጀቴ ባይቆርጥም
አይገለኝም ብትሄድ ፍቅር እንደ ውሀ ጥም
ካንተ መለየቱ ምን ሆዴን ቢያስብሰው
እህል አልጣ እንጂ ምበላው ምቀምሰው
ፍቅርን ተርቦ የለም የሞተ ሰው
በቃ ልሂድ ካልክ በቃ ሂድ በቃ
ታዲያ እስከመቼ ነፍሴ ተጨንቃ
አይንሳኝ እንጂ እድሜና ጤና
አንተን አጥቼ አልሞትም እና
አታስፈራራኝ
አታስፈራራኝ
አታስፈራራኝ
ከበቃህ ይብቃ
የምለምንህ ወድጄህ ወድጄህ አፍቅሬህ እንጂ
አትሂድ የምልህ ወድጄህ ወድጄህ አፍቅሬህ እንጂ
አንተን ካጣው መኖር የማልችል
ነብሴ በእጅህ ያለች ይመስል
ምነው ይሄን ያህል
ምነው ይሄን ያህል
ምነው ይሄን ያህል እንዴ
ምነው ይሄን ያህል
እንደ ውጥናችን ያኔ እንደጀመርነው
ተፈላልገን እንጂ ቢሆን ደስ የሚለው
ፍቅር በልመና የማይሆን ነገር ነው
አልዘልቀውምና ሁሌም ተማፅኜ
ለኔ እዳልተፈጠርክ ውስጤን አሳምኜ
ያላንተ መኖርን ልየው ደሞ ወስኜ
በቃ ልሂድ ካልክ በቃ ሂድ በቃ
ታዲያ እስከመቼ ነፍሴ ተጨንቃ
አይንሳኝ እንጂ እድሜና ጤና
አንተን አጥቼ አልሞትም እና
አታስፈራራኝ
አታስፈራራኝ
አታስፈራራኝ
ከበቃህ ይብቃ
አይንሳኝ እንጂ እድሜና ጤና
አንተን አጥቼ አልሞትም እና
አታስፈራራኝ
አታስፈራራኝ
አታስፈራራኝ
ከበቃህ ይብቃ