制作
出演艺人
Haile Roots
表演者
作曲和作词
Hailemichael Getnet Ayele
词曲作者
歌词
ኦዬ... ኦዬ... ኦዬ
የታመነ ነው አሀ
ያልሸነገለው አሀ
ያተርፋል ቃሉ አሀ
ከሚያሞግሰው አሀ
የታመነ ነው አሀ
ያልሸነገለው አሀ
ያተርፋል ቃሉ አሀ
ከሚያሞግሰው አሀ
መዋደድ ከሆነ ተደናንቆ
ሳይተራረሙ ተመራርቆ
አይደለም ይህ ፍቅር የእውነተኛ
የልብ ወዳጅ ከዋሸ ጓደኛ
ሳይነግረው ፊት ለፊት ሸነጋግሎት
እያየው ሊጠፋ እንዳላየ አልፎት
ከማያተርፍ ወዳጅ መስሎ መልካም
ይበልጣል የገሳጭ ቃል ባይደላም
የታመነ ነው አሀ
ያልሸነገለው አሀ
ያተርፋል ቃሉ አሀ
ከሚያሞግሰው አሀ
የታመነ ነው አሀ
ያልሸነገለው አሀ
ያተርፋል ቃሉ አሀ
ከሚያሞግሰው አሀ
መዋደድ ከሆነ ተደናንቆ
ሳይተራረሙ ተመራርቆ
አይደለም ይህ ፍቅር የእውነተኛ
የልብ ወዳጅ ከዋሸ ጓደኛ
ይለያል በቃሉ ለመዘነው
ወዳጁን ያልዋሸ የታመነው
ሳይሸነጋገል ቀርቦ እውነቱን
የሚኖር ተራርሞ ገልጦ የልቡን
ኦዬ... ኦዬ... ኦዬ
ያልሸነገለው
ወዳጅ የምለው
ሳይሸሽግ ውስጡን የሚገልጠው ነው
የሰመረለት ወዳጅ ላደለው
ከራስ ይበልጣል ከተወለደው
ኦዬ... ኦዬ
ኦዬ... ኦዬ
ያልሸነገለው
ወዳጅ የምለው
ሳይሸሽግ ውስጡን የሚገልጠው ነው
የሰመረለት ወዳጅ ላደለው
ከራስ ይበልጣል ከተወለደው
ኦዬ... ኦዬ
ኦዬ... ኦዬ
ከራስ ይበልጣል ከተወለደው
ከራስ ይበልጣል ከተወለደው
ከራስ ይበልጣል ከተወለደው
ከራስ ይበልጣል ከተወለደው
ያልሸነገለው
ወዳጅ የምለው (ኦ...)
ሳይሸሽግ ውስጡን የሚገልጠው ነው (ኦዬ)
የሰመረለት ወዳጅ ላደለው (ኦ...)
ከራስ ይበልጣል ከተወለደው (ኦዬ)
ያልሸነገለው
ወዳጅ የምለው
ሳይሸሽግ ውስጡን የሚገልጠው ነው
የሰመረለት ወዳጅ ላደለው
ከራስ ይበልጣል ከተወለደው
Written by: Hailemichael Getnet Ayele