制作

出演艺人
Mastewal Eyayu
Mastewal Eyayu
表演者
作曲和作词
Mastewal Eyayu
Mastewal Eyayu
词曲作者
Frezer Abebe Werq
Frezer Abebe Werq
作词
Mikael Hailu
Mikael Hailu
编曲

歌词

ኧረ አላት የደስ ደስ ጉብሏ
የአባይ ልጅ ናት ጠይም ሳዱላ
አረ አላት የደስ ደስ ጉብሏ
የአባይ ልጅ ናት እሷ ታድላ
እኸ ደርሳ እየቃኘች
እኸ ልቤን በፍቅሯ
እኸ ወዘወዘችኝ
እኸ የአባይ እንዚራ
የስለት ልጅ ሆነሽ (ባምባው ላይ ባምባው ላይ)
እናትሽ ማር ወልዳ (በላይ በላይ በላይ)
ኧረ እኔስ ገባሁኝ (ባምባው ላይ ባምባው ላይ)
አንቺን ወድጄ ዕዳ (በላይ በላይ በላይ)
የሰሩሽ ይመስል (ባምባው ላይ ባምባው ላይ)
ከአውታር ከእንዚራው (በላይ በላይ በላይ)
እንቅጥቅጥ አለልሽ (ባምባው ላይ ባምባው ላይ)
ያየሽ ሁሉ ሰው በላይ በላይ በላይ
ይዝመት ሰራዊት ይታወጅና
አያንስም ከሀገር የሷ ቁንጅና
ያዙላት ድባብ በሄደችበት
ሙሽራ እኮ ናት የአባይ ልጅ ማለት
የኔ አለም ቆንጆ ነሽ ስታምሪ
ውበትሽን ዘፈነው አዝማሪ
ብቅ አለች የበላይ ጦር ጋሻ
በሉላት አንገት በትከሻ
የኔ አለም ቆንጆ ነሽ ስታምሪ
ውበትሽን ዘፈነው አዝማሪ
ብቅ አለች የበላይ ጦር ጋሻ
በሉላት አንገት በትከሻ
ኧረ አላት የደስ ደስ ጉብሏ
የአባይ ልጅ ናት ጠይም ሳዱላ
አረ አላት የደስ ደስ ጉብሏ
የአባይ ልጅ ናት እሷ ታድላ
እኸ ደርሳ እየቃኘች
እኸ ልቤን በፍቅሯ
እኸ ወዘወዘችኝ
እኸ የአባይ እንዚራ
ደግሰሽ ቁንጅናን (ባምባው ላይ ባምባው ላይ)
ሁሉን ብትጠሪ (በላይ በላይ በላይ)
ግጥም አስጠፋሽው (ባምባው ላይ ባምባው ላይ)
ጎበዙን አዝማሪ (በላይ በላይ በላይ)
አባይ ገራገሩ (ባምባው ላይ ባምባው ላይ)
እኔ መረብ የለኝ (በላይ በላይ በላይ)
ይቺን ጠይም አሳ (ባምባው ላይ ባምባው ላይ)
ምነው ብትሸልመኝ (በላይ በላይ በላይ)
ይዝመት ሰራዊት ይታወጅና
አያንስም ከሀገር የሷ ቁንጅና
ያዙላት ድባብ በሄደችበት
ሙሽራ እኮ ናት የአባይ ልጅ ማለት
የኔ አለም ቆንጆ ነሽ ስታምሪ
ውበትሽን ዘፈነው አዝማሪ
ብቅ አለች የበላይ ጦር ጋሻ
በሉላት አንገት በትከሻ
የኔ አለም ቆንጆ ነሽ ስታምሪ
ውበትሽን ዘፈነው አዝማሪ
ብቅ አለች የበላይ ጦር ጋሻ
በሉላት አንገት በትከሻ
(የኔ አለም)
(ውብትሽን)
(ብቅ አለች)
(በሉላት)
(የኔ አለም)
(ውብትሽን)
(ብቅ አለች)
(በሉላት)
Written by: Frezer Abebe Werq, Mastewal Eyayu
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...