制作
出演艺人
Aster Abebe
表演者
作曲和作词
Aster Abebe
词曲作者
歌词
ጫካ አይወረድ እንጨትን ፍለጋ
ቤትህን ለመስራት እንዲሆንህ ማረፊያ
በወንድሞች ህብረት ፍቅር ትከብራለህ
ሁለት ሦስት ስንሆን በዚያ ትገኛለህ
መጠበቅ ነው እንጂ ማጥበቅ ሰንሰለቱን
ቀዳዳ አግኝቶ ክፉ እንዳይበትነን
አንዱ ወንድም ሲደክም መቆም ሲያቅተው
በፍቅር ደጋግፈን ምርኩዙ ከሆንነው የሚደፍረን ማን ነው
መጠበቅ ነው እንጂ ማጥበቅ ሰንሰለቱን
ቀዳዳ አግኝቶ ክፉ እንዳይበትነን
አንዱ ወንድም ሲደክም መቆም ሲያቅተው
በፍቅር ደጋግፈን ምርኩዙ ከሆነው የሚደፍረን ማን ነው
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
እግዚአብሔር ፍቅር
እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል
እግዚአብሄር ፍቅር
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
እግዚአብሔር ፍቅር
እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል
እግዚአብሔር ፍቅር
ፍቅር ይታገሳል አንተ እንደታገስከን
በሰፊው ትከሻህ እንደተሸከምከን
ቅድስናችን ነህ ጽድቃችን ባንተ ነው
በባዶ መኮፈስ መገበዙስ ለምን ነው?
ፈቃዱን ለሳተ ከመንገዱ ወጥቶ
ህመም ለጸናበት በጠላት ተመቶ
አንገቱን ነቅንቆ የአንተ ፍቅር አያልፍም
የወደቀን ማለፍ ባሕርይ አይደለም በዛ አትታወቅም
ፈቃዱን ለሳተ ከመንገዱ ወጥቶ
ህመም ለጸናበት በጠላት ተመቶ
አንገቱን ነቅንቆ ያንተ ፍቅር አያልፍም
የወደቀን ማለፍ ባሕርይ አይደለም በዛ አትታወቅም
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
እግዚአብሔር ፍቅር
እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል
እግዚአብሄር ፍቅር
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
እግዚአብሔር ፍቅር
እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል
እግዚአብሔር ፍቅር
የአዳምን እርቃን ደርሶ ከሸፈነው
የአባትነት ፍቅሩ አጋልጦ ካልሰጠው
ይህ ህይወት በኛ አለ ከተጠቀምንበት
ከራስ የሚያልፍ ፍቅር የተረፈ ህይወት
ማገገሙ አይቀረም ምህረቱ አክሞት
ወደ ጸጋው ዙፋን እንግፋው በጸሎት
የሌላውን እርቃን ተባብረን ስንሸፍን
ሞገስ አለ ከላይ የሚለቀቅልን በመያያዛችን
ማገገሙ አይቀረም ምህረቱ አክሞት
ወደ ጸጋው ዙፋን እንግፋው በጸሎት
የሌላውን እርቃን ተባብረን ስንሸፍን
ሞገስ አለ ከላይ የሚለቀቅልን በመያያዛችን
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
እግዚአብሔር ፍቅር
እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል
እግዚአብሄር ፍቅር
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
እግዚአብሔር ፍቅር
እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል
እግዚአብሔር ፍቅር
Written by: Aster Abebe