歌词
ያገር ቤት ወጣት ናት የተወደደች የተደነቀች
ጨዋነት ደግነት ፍቅር የተሞላች
ፍቅር የተሞላች
ደማም ናት ቀለመ ወርቅ ናት ያገር ቤቷ ልጅ
በቄጠማው መሃል እንደ ጠበል ፈልቃ
ነዶውን አቋርጣ በሰርዶ ተሰርቃ
ዋርካ ተከልላ ከአደይ እኩል ደምቃ
ነጥራ ታበራለች ትታያለች ጠልቃ
ዋልታ ለሰፈሩ አድማቂው ተተጠሪ
ደግነት ጨዋነት ሞልቷት አበዳሪ
አድጋ በውዳሴ ተመርቃ ኗሪ
ሸንጎ ፈረደላት ሳትሻ መስካሪ
ያገር ቤት ወጣት ናት የተወደደች የተመረቀች
ጨዋነት ደግነት ፍቅር የተሞላች
ፍቅር የተሞላች
ደማም ናት ቀለመ ወርቅ ናት ያገር ቤቷ ልጅ
ጤና አዳም ናት እሷ የጠራች ወለላ
በስንደዶ አጀብ የጎላች አለላ
ሀይቅ ዳር ተፈጥራ ከማማው ላይ ውላ
ቋጭታ ትሸኛለች ታፀድቃለች ገላ
ቡራኬ የተሰጣት ውበት የተቸረች
ሞያ የዘራባት በእምነቷ ያደረች
ትህትና ጌጧ ከድክመት የራቅች
ዳስ አንጣላ ሰርታ ፍቅር የዘከረች
ያገር ቤት ወጣት ናት የተወደደች የተወደደች
ጨዋነት ደግነት ፍቅር የተሞላች
ፍቅር የተሞላች
ደማም ናት ቀለመ ወርቅ ናት ባለሞያም ነች
እስኪ በይ ነይና ላጫውትሽ በቅጡ
መች ይበጃል ብለሽ ለብቻ ቢያጌጡ
ማተብና ኩታሽ አልቦሽ ጉልላቱ
ሳይሽ አደከመኝ የገላሽ ድምቀቱ
ስቴድ ስትቀመት ደግሞም ስትነሳ
ሲያዩያት የምታፈዝ ቀጭን ኩታ ለብሳ
መለከት ቢነፋ ቢጠራም ሰፈሩ
አድማቂ እንደ ኮኮብ እሷ ነች ላገሩ
መለከት ቢነፋ ቢጠራም ሰፈሩ
አድማቂ እንደ ኮኮብ እሷ ነች ላገሩ
Written by: Theodros Tadesse


