歌词
በነፍስህ ቢመጡ
ፍቅሬን ሳትለውጠው
ባለህም በሌለህ
ሾመህ ብታስቀምጠው
አብልጠኸው ከራስህ
ብትመርጠው
ነፍስህን ብትሰጠው
ንቆህ አዳለጠው
አብልጠኸው ከራስህ
ብትመርጠው
ነፍስህን ብትሰጠው
ንቆህ አዳለጠው
በሰጠኸው ፍቅር
ልቤ ተቀማጥሎ
ሹመት ንግሥናውን
አላውቅበት ብሎ
ጠግቦ ጌትነቱን
አልችል ብሎ
ሄደ ክብሩን ጥሎ
ከቤትህ ኮብልሎ
ጠግቦ ጌትነቱን
አልችል ብሎ
ሄደ ክብሩን ጥሎ
ከቤትህ ኮብልሎ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
አንተን መሳይ
ፈልጌ አጣሁ
አንተን መሳይ
ፈልጌ አጣሁ
ከኮበለለበት
ከሄደበት ስፍራ
ቢፈራረቁበት
ውርደት ከመከራ
ያን ጊዜ ፍቅርህን
ልኩን አውቋል
ይቅርታህን ናፍቋል
ልቤ ደጅህ ቆሟል
ያን ጊዜ ፍቅርህን
ልኩን አውቋል
ይቅርታህን ናፍቋል
ልቤ ደጅህ ቆሟል
ከማንም ከምንም
እንደምታስበልጠው
ቢመለስ ከቤትህ
ምህረት እንምትሰጠው
የአንተ ልብ እንደ እኔ
እንዳልሆነ
ልቤ ስላመነ
ምህረት ለመነ
የአንተ ልብ እንደ እኔ
እንዳልሆነ
ልቤ ስላመነ
ምህረት ለመነ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
አንተን መሳይ
ፈልጌ አጣሁ
አንተን መሳይ
ፈልጌ አጣሁ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
ዞሬ መጣሁ
አንተን መሳይ
ፈልጌ አጣሁ
አንተን መሳይ
ፈልጌ አጣሁ
አንተን መሳይ
አንተን መሳይ
አንተን መሳይ
አንተን መሳይ
አንተን መሳይ
አንተን መሳይ
አንተን መሳይ
Written by: Elias Woldemariam, Mikaya Behailu