音乐视频

音乐视频

制作

出演艺人
Daniel Amdemichael Amdemariam
Daniel Amdemichael Amdemariam
表演者
作曲和作词
Daniel Amdemichael Amdemariam
Daniel Amdemichael Amdemariam
词曲作者

歌词

አሃ
አሃ
አሃ
አሃ
አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው
አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ
በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር
እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር
የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ
በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ
ፀጋው በእምነት ሆኖ አድኖኛል
እግዚአብሔር በልጁ ሕይወትን ሰጥቶኛል
ሁሉ ተፈጸመ በመስቀሉ
በሰላም እንድኖር በዘለዓለም ፍቅሩ
ላመስግነው በዝማሬ ይኼን ታላቅ ጌታ
ከጨለማ ለነጠቀኝ ከዚያ ክፉ ቦታ
ለወደደኝ ብርሃኑን ላበራ በሕይወቴ
መልካም ዜማ ለእርሱ ይሁን ይክበር መድሃኒቴ
አምላክ አበጃጀው ዘለዓለሜን
አንድ ልጁን ሰጥቶ ክርስቶስ ብቃቴን
የዘለላእም ህብረት ከአብ ጋራ
አገኘሁ ልጅነት በክርስቶስ ስራ
ምሥጋናውን ልዘምረው ልናገር ወንጌሉን
ጌታ ኢየሱስ እንድሚያድን ላብስር ምስራቹን
የአምላክ ፍቃድ ኢኼ ሆኗል ሰዎች ሚያመልጡበት
በልጁ ደም በእግዚአብሔር ጽድቅ አምነው ሚድኑበት
አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ክስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው
አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ
በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር
እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር
የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ
በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ
ምሥጋና ለአምላክ ፍቅር ለታደገኝ
እግሬን ከጨለማ መንገድ መለሰልኝ
ብርሃንን አሳየኝ ቅዱስ ቃሉ
ተፈጸመ እንዳለ ጌታ በመስቀሉ
ባመሰግን ይበዛል ወይ እኔስ በየእለቱ
ቅኔን ብቀኝ ባሸበሸብ ብዘምር በቤቱ
እልልስ ብል በታላቅ ድምጽ ብጮህ እስከደስታ
ባጨበጭብ በመቅደሱ ለዚህ ክቡር ጌታ
አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ክስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው
አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ
በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር
እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር
የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ
በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ
አሃ
አሃ
አሃ
አሃ
Written by: Daniel Amdemichael Amdemariam, Samuel Alemu
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...