歌詞
አካሌ ሸግዬ ነይ
በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ
አካሌ ሸግዬ ነይ
ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ
እንደምን አድረሻል አንቺ አመለ ኩሩ
አማላይ ጠፋልሽ ባገር በመንደሩ
የማብሰልሰል ሚስጥር የሃሳብ ሹክሹክታ
መወያየት ሆኗል ገጥሞ ከትዝታ
መወያየት ሆኗል አዬ ገጥሞ ከትዝታ
የትከሻዬ ጌጥ የጫንቃዬ ጌታ
የዕምሮዬ ደባሽ ሸክሜ የትዝታ
ከየት ያደርሰኛል እግሬስ ብሄድበት
እታትረው ይዤ በትዝታ አቀበት
እታትረው ይዤ አዬ በትዝታ አቀበት
አካሌ ሸግዬ ነይ
ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ
አካሌ ሸግዬ ነይ
በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ
ተራመጅ በልቤ በለመድሽው መንገድ
ያንቺማ ትዝታሽ በፀብ አይታገድ
ቢፈርደኝ ምናለ ዳኛ ተሰይሞ
ቂመኛው ልቧማ አጠቃኝ አድሞ
ቂመኛው ልቧማ አዬ አጠቃኝ አድሞ
ፀብ ተራዱኝ አልል ወይ አላድብ ከሰው
እኔስ ያንቺን ፍቅር ወዴት ልካሰሰው
ድረሽ ልቀበልሽ እጆቼን ዘርግቼ
አልካስ በዳኛ አንቺን ረትቼ
አልካስ በዳኛ አሄ አንቺን ረትቼ
አካሌ ሸግዬ ነይ
በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ
አካሌ በዳመናው ላይ
ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ
ከፍቅርሽ ማቅ ወስዶ ልቤን ምን ቀበረው
ትዝታን ጎዝጉዞ ሲያስብሽ ያደረው
እደርሳለሁ እንጂ በየበራበሩ
አንቺ ካልተገኘሽ ምን ሊያምር ነገሩ
አንቺ ካልተገኘሽ አዬ ምን ሊያምር ነገሩ
የለሽ ካጠገቤ አይሎ ትዝታው
ይማፀንሽ ጀመር ምሶሶና ዋልታው
ውበትሽ ተወርቶ ሙግት ተነስቶበት
ተወራርጄአለሁ እንዳልረታበት
ተወራርጄአለሁ አዬ እንዳልረታበት
ይቅር ለምስክር እርቄ መሄዴን
በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
Written by: Elias Woldemariam, Yilma G/Ab


