積分
演出藝人
Abdu Kiar
演出者
詞曲
Abdu Kiar Kahssay
詞曲創作
Abdu Kiar
詞曲創作
歌詞
ምንድነህ አለችኝ ኧረ ምን ልበላት
ጥቁር ሀበሻነት ከፊቴ እየታያት
አታውቀኝ እንዳልል ስንት አሳልፈናል
ጠብቄያት ጠብቃኝ ፍቅርን ተካፍለናል
ምንነጋገርበት ቋንቋው አንድ አይነት
አዲስ ከተማ ነው የተማርንበት
ምንድነህ ትላለች መልሱልኝ ሀገር
እኔስ የሚገባኝ ሰው መሆኔ ነበር
ምንነጋገርበት ቋንቋው አንድ አይነት
አዲስ ከተማ ነው የተማርንበት
ምንድነህ ትላለች መልሱልኝ ሀገር
እኔስ የሚገባኝ ሰው መሆኔ ነበር
ሁሉም ውስጡ ስጋና ደም (ስጋና ደም ስጋና ደም)
ቀለም መልኩ ቢለያይም (ቢለያይም ቢለያይም)
በእናቱ አንድ ነው በአባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ አዳም ነው
ብዙ ተባዙ ሲል ሂዱ አለምን ሙሉዋት
እንድትመቸን አርጎ መሬትን ሲሰራት
እንዳንለያይ ነበር መፅሃፉም መውረዱ
መች ሀረግ ልንቆጥር ሆኖ አንድ የአዳም ግንዱ
ምንነቴን ወዳ ብታውቅ ማንነቴን
ቆጠራ ልግባ ወይ አያት ቅድመ አያቴን
ምንድነህ ብላለች ሰው ነኝ ልላት ነው
ነጭም ጥቁር በአለም ሁሉም የአዳም ልጅ ነው
እኔነቴን ወዳ ብታውቅ ማንነቴን
ቆጠራ ልግባ ወይ አያት ቅድመ አያቴን
ምንድነህ ብላለች ሰው ነኝ ልላት ነው
ነጭም ጥቁር በዓለም ሁሉም የአዳም ልጅ ነው
ሁሉም ውስጡ ስጋና ደም (ስጋና ደም ስጋና ደም)
ቀለም መልኩ ቢለያይም (ቢለያይም ቢለያይም)
በእናቱ አንድ ነው በአባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ አዳም ነው
ሁሉም ውስጡ ስጋና ደም (ስጋና ደም ስጋና ደም)
ቀለም መልኩ ቢለያይም (ቢለያይም ቢለያይም)
በእናቱ አንድ ነው በአባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ አዳም ነው
Written by: Abdu Kiar, Abdu Kiar Kahssay