積分

演出藝人
Michael Belayneh
Michael Belayneh
演出者
詞曲
Michael Belayneh
Michael Belayneh
詞曲創作
Michael Belayneh Hailu
Michael Belayneh Hailu
詞曲創作
製作與工程團隊
Michael Belayneh
Michael Belayneh
製作人

歌詞

የነበረውን ቃል ከማስታወስ በቀር
ሁሉን እያወቅነው እኔ ምን ልናገር
አብሮ ያከረመን የፍቅር ማህተም
እሄዳለሁ ያልሽ እለት ጀመረ ሊታመም
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በልቦናችን ያደረ
ከአይን ርቆ የሠፈረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በፍቅራችን የከበረ
በመግባባት የሠመረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
አውቃለሁ ምስኪን ናት ሀገርሽ ሀገሬ
የተገናኙባት ፍቅርሽና ፍቅሬ
ማን አለ ያላየን አሻጋሮ ከማዶ
አይቻል ሆኖ እንጂ ፍቅር ሁለት ወዶ
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በልቦናችን ያደረ
ከአይን ርቆ የሠፈረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በፍቅራችን የከበረ
በመግባባት የሠመረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
ምስክር ላንጠራ ላይኖረን አስረጂ
ውርስ አለን ቀድሞውን አብረን ልናረጅ
እኛ ነን ወይ ፍቅር ዛሬ የተረታ
ኑሮአችን እያደር ባገር ሲበረታ
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በልቦናችን ያደረ
ከአይን ርቆ የሠፈረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በፍቅራችን የከበረ
በመግባባት የሠመረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
አይተናል ቀናቱ ሳምንትና ወሩ
ሲለያዩላቸው ልብን እንደሚሠብሩ
ውሀ እንደነፈጉት የደጃፍ አበባ
ፍቅራችን በጥማት ሞቶ እንዳናነባ
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በልቦናችን ያደረ
ከአይን የሠፈረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በፍቅራችን የከበረ
በመግባባት የሠመረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
ቃል ነበረን ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በልቦናችን ያደረ
ከአይን ርቆ የሠፈረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን ቃል ነበረን
ቃል ነበረን ቃል ነበረን
በፍቅራችን የከበረ
በመግባባት የሠመረ
ቃል ነበር ቃል ነበረን
Written by: Michael Belayneh, Michael Belayneh Hailu
instagramSharePathic_arrow_out

Loading...