album cover
Woyzerit
album cover
Woyzerit 由 ela records 於 2025年10月1日發行,收錄於專輯《WIHA ENA ESAT - ESAT》中
2025年10月1日
標籤ela records
BPM
旋律
原聲音質
Valence
節奏感
輕快

歌詞

ሁሉን ፈላጊ የራሱን ያጣል
ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት ይላሉ
(ጨዋታው አለው አደጋ)
ለሷ የሚገባት ይመስላታል ያየችው ሁሉ
(አታርፍ ሁሌ ሌላ ፍለጋ)
አንዴ ሰከን ልንገራት ልኳን
ወይዘሪት፣
ዋስተና የለኝ ባንቺ ቀድሞም
መለየትሽ ከኔ ቢጎዳኝም
ያበረታኛል አይገለኝም
ወይዘሪት፣
ከማን ገባ ዛሬ ደሞ
የለውም ልብሽ ቋሚ ማረፊያ
ሁሉንም አርጎ መተላለፊያ
የለውም ልብሽ ቋሚ ማረፊያ
ተማርኮ በወከባ በግፊያው
ካየው ሁሉ ዓይንሽ ይዞ ፍለጋ
ከጎንሽ ካለው ሰው ልብሽ ሳይረጋ
ስታርፊ ከሌላው ልቡን ይዘሽ ያንዱን
አላየው አላየው ይሄኛው ጉዱን
አርገሽው ውድድር አንዱን ከሌላ
ፍላጎቱ ግን ልብሽ መቼም ላይሞላ
ለሰጠሁሽ ፍቅር ሁሉ ነፍገሽ ምላሽ
ምን ቀረኝ ምን ቀረኝ ከባዶ ገላሽ
ኋላ አንቺን ነው ቢሉ አተራማሽ
እንደ ቢራቢሮ ነሽ ዞሮ ሁሉንም ቀማሽ
ብትመለሽ ብዬ ብጠብቅም ጭራሽ
አስቀምጧል ብዙ ሰው ልብሽ እንደ አዳራሽ
ይቅርታ ወይዘሪቷ
ብሰጥሽም ልቤን ባለን ቆይታ
ላይሆነኝ አማላጅ ያ ውብ ፈገግታ
ጥለሽኝ ሄድሽ በባዶ ሳይኖርሽ ደንታ
ዋስ ዋስ መች ይሆን እንደራስ
አስጠናችው ልቤን ደጇን ብላ ይባስ
ዋዛ ዋዛ ጨዋታ ነው ለሷስ
መቀበል እንጂ መች መስጠት አውቆ ልቧስ
ያዢው በእጅሽ ያለውን አጥብቀሽ፣
የራስን መያዝ ጠበቅ አድርጎ
ስሜቱን ከልብሽ ጠብቀሽ፣
እንደ መዝገን ነዋ ጉም
የፈለግሽው ሁሉ ላይሆን ያንቺ፣
ፍለጋ ፍለጋ ብቻ በባዶ
ይልቁን የራስሽን እንዳታጪ፣
ይሻላል መጠንቀቁ - አይሻልም ወይ?
ሲሻት አኩራፊ
ታሪኳን የሰማው ዕውር ደጋፊ
ከወጥመዷ አይተርፍ ዒላማዋ ሰፊ
እንደ ነዳጅ ማደያ ሰው በሰው ደርቦ ሁሌ አሰላፊ
ዛሬ ሩቅ ሆኖ በሱ የሚስቀው
ነገ ከእግሯ ስር ይገኛል ሳያውቀው
እስኪሰማው ምቾት የዋና አባወራ
ቆይተው ግን ራሷ እስኪያልፍ የሱ ተራ
ያዢው በእጅሽ ያለውን አጥብቀሽ፣
የራስን መያዝ ጠበቅ አድርጎ
ስሜቱን ከልብሽ ጠብቀሽ፣
እንደ መዝገን ነዋ ጉም
የፈለግሽው ሁሉ ላይሆን ያንቺ፣
ፍለጋ ፍለጋ ብቻ በባዶ
ይልቁን የራስሽን እንዳታጪ፣
ይሻላል መጠንቀቁ - አይሻልም ወይ?
ወይዘሪት፣
ዋስተና የለኝ ባንቺ ቀድሞም
መለየትሽ ከኔ ቢጎዳኝም
ያበረታኛል አይገለኝም
ወይዘሪት፣
ከማን ገባ ዛሬ ደሞ
የለውም ልብሽ ቋሚ ማረፊያ
ሁሉንም አርጎ መተላለፊያ
የለውም ልብሽ ቋሚ ማረፊያ
ተማርኮ በወከባ በግፊያው
ካየው ሁሉ ዓይንሽ ይዞ ፍለጋ
ከጎንሽ ካለው ሰው ልብሽ ሳይረጋ
ስታርፊ ከሌላው ልቡን ይዘሽ ያንዱን
አላየው አላየው ይሄኛው ጉዱን
አርገሽው ውድድር አንዱን ከሌላ
ፍላጎቱ ግን ልብሽ መቼም ላይሞላ
ለሰጠሁሽ ፍቅር ሁሉ ነፍገሽ ምላሽ
ምን ቀረኝ ምን ቀረኝ ከባዶ ገላሽ
ኋላ አንቺን ነው ቢሉ አተራማሽ
እንደ ቢራቢሮ ነሽ ዞሮ ሁሉንም ቀማሽ
ብትመለሽ ብዬ ብጠብቅም ጭራሽ
አስቀምጧል ብዙ ሰው ልብሽ እንደ አዳራሽ
ያዢው በእጅሽ ያለውን አጥብቀሽ፣
የራስን መያዝ ጠበቅ አድርጎ
ስሜቱን ከልብሽ ጠብቀሽ፣
እንደ መዝገን ነዋ ጉም
የፈለግሽው ሁሉ ላይሆን ያንቺ፣
ፍለጋ ፍለጋ ብቻ በባዶ
ይልቁን የራስሽን እንዳታጪ፣
ይሻላል መጠንቀቁ - አይሻልም ወይ?
ያዢው በእጅሽ ያለውን አጥብቀሽ፣
የራስን መያዝ ጠበቅ አድርጎ
ስሜቱን ከልብሽ ጠብቀሽ፣
እንደ መዝገን ነዋ ጉም
የፈለግሽው ሁሉ ላይሆን ያንቺ፣
ፍለጋ ፍለጋ ብቻ በባዶ
ይልቁን የራስሽን እንዳታጪ፣
ይሻላል መጠንቀቁ
አይሻልም ወይ?
Written by: Jonny Ragga
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...