歌詞
የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ
ቁጭ ብለሽ እናውጋ
የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ
ልምጣ ልከተልሽ ወይ
መቶ ሰው ቢሰለፍ አንቺን የማይመስለኝ
ፍቅር ነው ህመም ነው በይ እስኪ ንገሪኝ
አንቺን ባየሁበት ሌላ አልታይ ቢለኝ
ጠረጠርኩት ልቤን ተነካሁ መሰለኝ
ተነካሁ መሰለኝ
በወር በአስራ አምስት ቀን ከሆነ ነገሩ
ሳላይሽ አልቀርም ይብዛ እንጂ ችግሩ
ሰውነቴም ከሳ ልቤም ተጨነቀ
ናፍቆቴም አልወጣ ፍቅሬም አላለቀም
ፍቅሬም አላለቀም
የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ
ቁጭ ብለሽ እናውጋ
የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ
ልምጣ ልከተልሽ ወይ
መንገዱ ቀጥታ የለው ጎርበጥባጣ
ደርሷል ለማቀፍም ያቺን ልጅ ብትመጣ
ቀኑን አብረን ውለን አብረን ስንለያይ
የቀረሽ መሰለኝ ዓይንሽን የማላይ
ዓይንሽን የማላይ
ሲጫወቱ ማማር ሲለብሱ መድመቅ
ውብ እንደሷ ቆንጆ አይቼም አላውቅም
አንቺ አለሽኝ ብዬ ጠልቼ ሁሉን
እንደምን ከርታታ ብቸኛ ልሁን
ብቸኛ ልሁን
የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ
ቁጭ ብለሽ እናውጋ
የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ
ልምጣ ልከተልሽ ወይ
ካጠገቤ ሆና ትጫወት ትሳቅ
ከጥርሶቿ መሃል አለ የሚናፈቅ
አልሰማ አልኩኝ እንጂ ልቤ የሚነግረኝን
አሁን መች አጣሁት ለኔ የሚሆነኝን
ለኔ የሚሆነኝን
ካጠገቤ ሆና ትጫወት ትሳቅ
ከጥርሶቿ መሃል አለ የሚናፈቅ
አልሰማ አልኩኝ እንጂ ልቤ የሚነግረኝን
አሁን መች አጣሁት ለኔ የሚሆነኝን
ለኔ የሚሆነኝን
ለኔ ለኔ
ለኔ የሚሆነኝን ለኔ የሚሆነኝን
ለኔ የሚሆነኝን ለኔ የሚሆነኝን
Written by: Tesfaye Lemesa