album cover
Wuletash Alebign
4,642
World
Wuletash Alebign 由 Nahom Records Inc 於 2007年8月25日發行,收錄於專輯《Best of Neway Debebe Collection》中
album cover
發行日期2007年8月25日
標籤Nahom Records Inc
語言English
旋律
原聲音質
Valence
節奏感
輕快
BPM

音樂影片

音樂影片

歌詞

ውለታሽ አለብኝ ልከዳሽ አልወድም
ስምሽን በቁም ነገር አነሳለሁ የትም
የክፉ ቀን ጓዴ ብልሽ እወዳለው
ብድር መላሽ ያድርገኝ አመሰግናለው
ያን ጊዜ ስቸገር ጨለማ ሲውጠኝ
ወዳጄን ጠላቴን መለየት ሲያቅተኝ
ፈጥነሽ ደረሽልኝ ፍቅር አልጎደለብሽ
የክፉ ቀን ጓዴ መመስገን አለብሽ
የውለታ ጉዳይ ውለታ ነው መልሱ
የተሳካ ለታ ከቀኑ ሲደርሱ
ይሙላልኝ በማለት ከርሚያለው ስመኝ
ብድር ለመመለስ እላለው ቀን ይስጠኝ
ወዳጄ እንደምን ነሽ
አለኝታዬ እንዴት ነሽ
አለኝታዬ እንዴት ነሽ
አመሰግናለው
ውለታሽ አለብኝ ልከዳሽ አልወድም
ስምሽን በቁም ነገር አነሳለሁ የትም
የክፉ ቀን ጓዴ ብልሽ እወዳለው
ብድር መላሽ ያድርገኝ አመሰግናለው
ኩምነገር ደግነት መልካም ምግባሮችሽ
ከሀውልት ጠንክረው ቆመው ሲያበሩልሽ
ከልቤ መሀደር ስፍራም ሳይጠባቸው
በክብር ተቀምጠው አሉ ህያው ናቸው
ከውለታም ደግሞ ውለታ ነው እንጂ
ችግር ሲያፋጥጠኝ ስትሆኚኝ ቀኝ እጅ
የደግነት ንግስት ብልሽ ምን ያንስሻል
የዘላለም ሀውልት ከልቤ ተክለሻል
ወዳጄ እንደምን ነሽ
አለኝታዬ እንዴት ነሽ
የኔ ኮንጆ እንዴት ነሽ
አመሰግናለው
ወዳጄ እንደምን ነሽ
አለኝታዬ እንዴት ነሽ
የኔ ኮንጆ እንዴት ነሽ
መመኪያዬ እንዴት ነሽ
ወዳጄ እንደምን ነሽ
አለኝታዬ እንዴት ነሽ
የኔ ኮንጆ እንዴት ነሽ
መመኪያዬ እንዴት ነሽ
ወዳጄ እንደምን ነሽ
አለኝታዬ እንዴት ነሽ
የኔ ኮንጆ እንዴት ነሽ
መመኪያዬ እንዴት ነሽ
ወዳጄ እንደምን ነሽ
Written by: Neway Debebe
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...