Lyrics

ፍቅርሽ አንድ አንድ እያለ ልቤ ውስጥ ተደላደለ ተደላድሎስ መቼ ቀረ? ያስተክዘኝ ጀመረ ስትጠፊ የሚያስጨንቀኝ በሀሣብ የሚያንፏቅቀኝ ልንገርሽ ውዴ መውደዴ ፍቅርሽ ነው ሰሞኑን ጉዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ አቤት የኔ ነገር ይገርማል ለጤና ያርግልኝ ጌታዬ ምነው ቢቀርብኝ እላለሁ ሲበዛ ጭንቀቴ ስቃዬ ደሞ ደስታሽን ሳየው በዓይኔ ሀሳቤን እረሳና ድካሜን ጭራሽ ጣፍጦኝ ቀረ ስቃዬ ወደድኩት ወደድኩት ህመሜን ሰው ህመሙን ወዶ፤ ሰው ስቃዩን ወዶ እንዴት ነው የሚኖረው እንዴት ነው የሚዘልቀው ሰው ገዳዩን ወዶ ፍቅር እንዲህ አይደል ወይ ታምኖ መገኘት የወደዱትን ሰው ያፈቀሩትን ሰው ሲደሰት ማየት ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ፍቅርሽ አንድ አንድ እያለ ልቤ ውስጥ ተደላደለ ተደላድሎስ መቼ ቀረ? ያስተክዘኝ ጀመረ ስትጠፊ የሚያስጨንቀኝ በሀሣብ የሚያንፏቅቀኝ ልንገርሽ ውዴ መውደዴ ፍቅርሽ ነው ሰሞኑን ጉዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ እንዳልቀየምሽ አርጎኛል- ቂም እንዳልይዝብሽ አርጎኛል ልቤ ፍቅርን አምኖ ሁልጊዜ ልክ ናት ልክ ናት ይለኛል ምታመመው በፍቅርሽ ሆኗል ምድነውም በፍቅርሽ ሆኗል አዕምሮዬም ብዙ እያለመ ሰሞኑን እንደማይሆን ሆኗል ህልምን እኔ ሣውቀው ሌሊት በማታ ነው ወይ... ጉዴ ሰሞኑን ከእንቅልፌ የምነቃው አንቺን ለማለም ነው እንደዚህ የምሆነው ለምን ይመስልሻል ስለወደድኩሽ ነው ስላፈቀርኩሽ ነው መቼ ይጠፋሻል ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ ወይ ጉዴ አንቺን መውደዴ
Writer(s): Abdu Kahssay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out