Lyrics

ፍቅርሽ እንደጥላ እንደጥላ ሲቀርቡት ይርቃል ደሞ ቁርጥ አርገዉ ሲተዉት ዞሮ ይናፍቃል ዛሬ አገኘሁሽ ስል ሲነጋ የለሽም ከጐኔ ላም አለኝ በሰማይ ሆነብኝ ያንቺስ ፍቅር ለኔ እንደዉ የአንቺን ነገር ሳስበዉ አንዳንዴ ግራ ይገባኛል ግርም ይለኛል ድንግር ይለኛል የማደርገዉ ሳጣ ትቅርብኝ እልና ልቤ አልቆርጥ ይለኛል አልቆርጥ ይለኛል አልቆርጥ ይለኛል አንድ ሰሞን መተሸ ተስፋ እየመገብሽኝ አለዉ ትይኝና አለዉ ትይና ታጓጉኚና ደሞ ለአንድ ሰሞን ታስጨንቂኛለሽ ጠፍተሸ እንደገና ደሞ እንደገና ደሞ እንደገና አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ ፍቅርሽ እንደጥላ እንደጥላ ሲቀርቡት ይርቃል ደሞ ቁርጥ አርገዉ ሲተዉት ዞሮ ይናፍቃል ዛሬ አገኘሁሽ ስል ሲነጋ የለሽም ከጐኔ ላም አለኝ በሰማይ ሆነብኝ ያንቺስ ፍቅር ለኔ በቃ ሄደች ብዬ ቀን አንቺን ለመርሳት ሳስብ ሳመነታ ቀን ሳመነታ ቀን ሳመነታ ባላሰብኩት ሰዓት ምነዉ ጠፋህ ብለሽ ትመጫለሽ ማታ የማታ ማታ የማታ ማታ ተወደድኩኝ ብለሽ ከሆነም ነግረሽኝ ባዉቀዉ ይሻለኛል ባቅ ይሻለኛል ባዉቅ ይሻለኛል ፍቅርሽ ሲያስመርረኝ ምን አልባት አንድ ቀን ሆድ ይቆርጥልኛል ይቆርጥልኛል ይቆርጥልኛል አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅርስ ዕዳ አንዱ ብቻ ሲጐዳ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅርስ ዕዳ አንዱ ብቻ ሲጐዳ አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅርስ ዕዳ አንዱ ብቻ ሲጐዳ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅርስ ዕዳ አንዱ ብቻ ሲጐዳ
Writer(s): Tsehaye Yohannes Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out