Music Video

Credits

PERFORMING ARTISTS
Mahmoud Ahmed
Mahmoud Ahmed
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Mahmoud Ahmed
Mahmoud Ahmed
Composer
ሸዋሉል መንግሥቱ
Writer

Lyrics

ትናንትናን ጥሶ ዛሬን ተንተርሶ ነገንም ተውሶ አምናንም አፍርሶ ይመጣል ትዝታሽ ጏዙን አግበስብሶ ይመጣል ትዝታሽ ጏዙን አግበስብሶ ፍቅርንስ ሸኘሁት ወጥቼ እስከ ደጅ መውደድን ሸኘሁት ወጥቼ እስከ ደጅ ማባረር ያቃተኝ ትዝታን ነው እንጅ ማባረር ያቃተኝ ትዝታን ነው እንጅ ጎን ለጎን ሲሆን ፍቅር ነው ደስታ አበሳ አስቆጣሪው የተለዩ ለታ አልገባኝም እኔ ምንድን ነው ትዝታ አልገባኝም እኔ ምንድን ነው ትዝታ ትዝታ ነው አሉን የሀሳብ መርከቡ ትዝታ ነው አሉን የጭንቀት መርከቡ ማራገፊያውማ እኔ ነኝ ወደቡ ማራገፊያውማ እኔ ነኝ ወደቡ ምንኛ ባጠረ እድሜው የፍቅር መዝገበ ቃላቱ ትዝታ ባይኖር የትዝታን ዳገት ወጣሁት ተክዤ የትዝታን ዳገት ወጣሁት ተክዤ በእጄ ምናምኑን በልቤ አንቺን ይዤ በእጄ ምናምኑን በልቤ አንቺን ይዤ የምትራመዱ እንደተመቻችሁ አጅሬ ትዝታ ያልደረሰባችሁ እስኪ አውሱኝ ለኔ ደህና ልብ ያላችሁ እስኪ አውሱኝ ለኔ ደህና ልብ ያላችሁ በልቼ እርቦኛል ጠጥቼ ጠምቶኛል ሌሊት እየመጣ እንቅልፍ ይነሳኛል ጠላቴ ትዝታን ማን ሰው ያስጥለኛል ጠላቴ ትዝታን ማን ሰው ያስጥለኛል ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ
Writer(s): Mahmoud Ahmed Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out