Lyrics

እያዋለ ስሜን (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ከሰው አፍ ሊያበዛ (አይ ኩርፊያ አይ አመል) አውቆታል መሰለኝ ልቤን እንደገዛው ይናፍቀኝ ጀመር ኩርፍያው ከነ ለዛው (አይ ኩርፊያ አይ አመል) (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ተቆራኝቷልና ከአካል ከመንፈሴ ላሽሞንሙነው የእኔን መውደድ እንደራሴ ልቤ ሰፍ አታርገኝ ይመጣል በጊዜ እያለም አልቻልኩት የፍቅሩን አባዜ በቀላል ፣ በመልካም ፣ በቀላል ካሰብኩት ሲመሻሽ ብቅ ይላል እያልኩኝ እራሴው ሳወራ ለራሴው የፍቅር ፀጋህን ወደድኩት ኩርፊያህን (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ይናፈቅ ጀመር እያደር (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ይወደድ ጀመር ይፈቀር (አይ ኩርፊያ አይ አመል) (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ያመኑት ሰው እንከን ባይወጣም በጥድፊያ ካዳም ልጅ ፀባይ ላይ መች ይታጣል ኩርፊያ ከህመሙም በላይ ለሀሳብ ከመስጠቱ ፍቅር ነው የታየኝ በልጦ ከቅብጠቱ በቀላል ፣ በመልካም ፣ በቀላል ካሰብኩት ሲመሻሽ ብቅ ይላል እያልኩኝ ጠርጥሬው ቀስ በቀስ ጀምሬው አረፍኩት ለምጄ ኩርፊያህን ወድጄ (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ይናፈቅ ጀመር እያደር (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ይወደድ ጀመር ይፈቀር (አይ ኩርፊያ አይ አመል) (አይ ኩርፊያ አይ አመል) (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ፍቅር ነው ፣ ፍቅር ነው ፍቅር ሲያሰቃየው (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ካመሉ ቀን በቀን ከኩርፊያው የማያውቅ (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ይናፈቅ ጀመር እያደር (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ይወደድ ጀመር ይፈቀር (አይ ኩርፊያ አይ አመል) ይናፈቅ ጀመር ፣ ይናፍቅ ጀመር (አይ ኩርፊያ አይ አመል) (አይ ኩርፊያ አይ አመል)
Writer(s): Samuel Alemu, Wendeson Yihub Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out