Lyrics

ይህንን ፍቅር የሚጥም ስጦታ በከንቱ አትየው አታመንታ ላፍታ ንፁህ ነው ልቤ ብታምንም ባታምንም ሳትፈልግ ብትቀር እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም ለምን ልጠራጠር ለምንስ ልስጋ ባንተ ላይ በገዛ ፍቅሬ በዝምታ ድምበር ኧረ እንዴት ልኑር ባንተ ታጥሬ የሚዘገይ ተስፋ ማሳዘኑ አይቀር ልቦና እጅግ ሰባብሮ እኔ የለሁበትም ቢገባህ መልካም ፍቅሬ ውሎ አድሮ የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም እንዴት ሳልጠይቅህ ብዬ እንዳይቆጨኝ መስውአት ሆኛለሁና ጥፋትክን አይቼ መኖር አልችልም ብዙ ነው እና ልብህ ሰነፍ አይሁን ምንጊዜም ምክር ወዳጄ ተግሳፅ አትጥላ ኋላ አስጨክነኸኝ የለሁበትም ብሆን የሌላ የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም ይህንን ፍቅር የሚጥም ስጦታ በከንቱ አትየው አታመንታ ላፍታ ንፁህ ነው ልቤ ብታምንም ባታምንም ሳትፈልግ ብትቀር እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም የጋራ ነው ሲባል ሁሉም አምኖበት ተዋዶ አብሮ እየኖረ ምነው በኔ ብቻ ወድቆብኝ ፍቅር ሚዛኑ ዞረ ትጋቴ ነው ሀብቴ አንተን ለማረም ጊዜዬን ሰጥቼሀለሁ ላይ ላዩን እየኖርን ካልተረዳኸኝ ምን አደርጋለሁ የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም የለሁበትም እኔ የለሁበትም ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
Writer(s): Elias Woldemariam, Abrishe Zeget Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out