album cover
Endet
album cover
Endet è stato pubblicato il 23 agosto 2024 da Michael Belayneh come parte dell'album And Qal አንድ ቃል
23 agosto 2024
EtichettaMichael Belayneh
BPM93
Melodicità
Acousticità
Valence
Ballabilità
Energia

Testi

እንዴት ዐይኔን አልከልልም
እንዴት ልቤን ተው አልልም
እንዴት በቃኝ ብዬ አልምልም
እንዴት ባንቺ እኔ አልጨክንም
እየታየ እምቢታሽ ዕድሜዬን ሲያነክት
በማያረጅ ልቤ መጠበቅ አይታክት
ምን ዐይነት መፍቀድ ነው ዐቅም የሚሰባብር
አለኹ ለማትወጂኝ ተስፋዬን ስገብር
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
ፊት እየነሳሽኝ ልቤ አልደነደነም
ሽሽትሽ እንድቆርጥ ምክንያት አልኾነም
እወደው ሥራ ዐጣኹ አንቺን እንደመሣል
እንዴት ገዳዩ ደጅ ሰው ይመላለሳል
እንዴት እንዴት
እያለ በንዴት
ልቤ ሲነድ ዋለ
ተላላ እንደኔ ማን አለ
እንዴት ዐይኔን አልከልልም
እንዴት ልቤን ተው አልልም
እንዴት በቃኝ ብዬ አልምልም
እንዴት ባንቺ እኔ አልጨክንም
ነጻ አልወጣ አልኩ እንጂ ተስፋን ተላቅቄ
መገፋቴንማ አውቃለሁ ጠንቅቄ
መውደድ ጸጋም ቢኾን ለልብ የሚታደል
ወድጄ አስጨንቄሽ አልፈጽምም በደል
የስሜት ስካር ነው ፍቅር ሌላ ስሙ
ወድቆ መቅረት አለ ጸንቶ እንደመቆሙ
እንዴት አልጨክንም ብልም እየከፋኝ
ካጉል ተስፋ እሚያስጥል አንዳች መላ ጠፋኝ
ጠፍቼ ሞከርኩት እንዳላይሽ ምዬ
መጥቼም አየኹት ይሉኝታዬን ጥዬ
እንዳው ድካም ኾነ በተስፋ መጠውለግ
ሰላሜ አልተገኘም ቢፈለግ ቢፈለግ
Written by: Mesfin Weldetnsaye, Michael Belayneh
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...