album cover
Jegna
11.037
African
Jegna è stato pubblicato il 26 agosto 2022 da ela records come parte dell'album Jegna - Single
album cover
Data di uscita26 agosto 2022
Etichettaela records
Melodicità
Acousticità
Valence
Ballabilità
Energia
BPM86

Crediti

Testi

አላዝን አላዝን ግልፁን ልንገርሽ
ወኔ አጥቼ አይደለም የታማሁብሽ
ከንቱ ቢለፈልፍ ተናግሮ አናጋሪ
የወደደ አይደለም የጠላ ነው ፈሪ
ኧረ አይደለሁም አይደለሁም ደህና
ደካማ ጎኔን በአንቺ አዩብኝና
ስሜ ላይ ሄዱ ጎዝጉዘው እንደሳር
የወደቀ ዛፍ መቼ ያጠዋል ምሳር
ቀን የሰጠው ለታ ቅል ድንጋዩን ሰብሮ
ወትሮስ እንደ ጀግና ያውቃል ወይ ፎክሮ
አገኘሺኝ እንጂ ድንገት ስዘናጋ
ባልቆጨኝ ለፍቅርሽ የከፈልኩት ዋጋ
ሳስበው ሳሰበው ገባኝ ሳዳምጠው ውስጤን
ሽንፈት አልለውም በቃ በአንቺ መበለጤን
እንኳን ሰው ደካማዉ ቀርቶ የፈጠረው ጌታ
ተስሞ ተሸጧል በወዳጁ ማታ
ፍቅርን ብዬ እንጂ የምተናነሰው
ከመረረማ በእኔ ሚብሰው
ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ
ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ
ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ
ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ
አላዝን አላዝን ግልፁን ልንገርሽ
ወኔ አጥቼ አይደለም የታማሁብሽ
ከንቱ ቢለፈልፍ ተናግሮ አናጋሪ
የወደደ አይደለም የጠላ ነው ፈሪ
ኧረ አይደለሁም አይደለሁም ደህና
ደካማ ጎኔን በአንቺ አዩብኝና
ስሜ ላይ ሄዱ ጎዝጉዘው እንደሳር
የወደቀ ዛፍ መቼ ያጠዋል ምሳር
ባልጨክን ነው እንጂ ፊቱን በአንቺ ጉዳይ
ቤቴን ባልጎበኘው አሳስቆ ገዳይ
ወዶ መለየትን ቢመርም ልቅመሰው
ከእንግዲህ ውለታን አልጠብቅም ከሰው
ብቻ ቀርቦ ጉርሻ ልምዱም ባልኩራራበትም
ሰው ራቀኝ ብሎ መቼም እጅ አፉን አይስትም
ለምን ስል ልከፋ ደሞ ልዘን ምን በወጣኝ
አንድ አንቺን ነው እንጂ ሀቄን አያሳጣኝ
ፍቅርን ብዬ እንጂ የምተናነሰው
ከመረረማ በእኔ ሚብሰው
ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ
ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ
ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ
ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ
ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ
ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ
ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ
ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ
Written by: Mastewal Eyayu
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...