歌詞

መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ መቼም መተው መርሳት አያውቅበት ሆዴ ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው ማን አለኝ እንዳንቺ ነፍሴን የወረሰው ኮከብ ተገለጠ አዬ ተሸኘ ፀሀይ ልቤ ረጋ ሳይል አይኔ ሰው ሳያይ እሷም አልተገኘች አዬ ብደክም ብለፋ ፍቅሬስ አቦል ነበር አጣጪው ባይጠፋ መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ መቼም መተው መርሳት አያውቅበት ሆዴ ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው ማን አለኝ እንዳንቺ ነፍሴን የወረሰው የመውደዴን ሚስጥር አዬ እንዴት ልሸፍነው መናገር ይወዳል መለየት ክፉ ነው አንቺም አየሁ ጉድሽን አዬ መቼ ተነፈሽው ዝም ብለሽ አይደል ወይ ጥለሺኝ የሄድሽው መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ መቼም መተው መርሳት አያውቅበት ሆዴ ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው ማን አለኝ እንዳንቺ ነፍሴን የወረሰው ብርዱ እየበረታ አዬ በግንቦት በሰኔ ምነው በክረምቱ ትርቂያለሽ ካይኔ እስኪ ልሂድ ገዳም አዬ ልግባ ልመልኩሰው ላንቺስ እርምም የለሽ ትደርሻለሽ ከሰው ትደርሻለሽ ከሰው ትደርሻለሽ ከሰው
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out