歌詞

መጠሪያ አልተገኘም የሚሆንሽ ላንቺ ተስማምቶ ቁንጅና እራሱ ነሽ ውበት ነፍስ ህይወትን ዘርቶ መጠሪያ አልተገኘም የሚሆንሽ ላንቺ ተስማምቶ ቁንጅና እራሱ ነሽ ውበት ነፍስ ህይወትን ዘርቶ አለተፈጠረም ሰው የለሽም አምሳያ የቁንጅና ጣርያ የውበት ማሰሪያ በሰፈሩ ሁሉ የሚያማምር ሞልቶ ውበትሽ እንደ አርማ የሚታየው ጎልቶ የንግስት ግርማ አለሽ አንገት የሚያስደፋ ቃልሽ ምስክር ነው እውነት እንዳልጠፋ ቢፈጠር ርቀት ከሰማይ ሰማይ እመጣ ነበር አይንሽን እንዳይ መጠሪያ አልተገኘም የሚሆንሽ ላንቺ ተስማምቶ ቁንጅና እራሱ ነሽ ውበት ነፍስ ህይወትን ዘርቶ መጠሪያ አልተገኘም የሚሆንሽ ላንቺ ተስማምቶ ቁንጅና እራሱ ነሽ ውበት ነፍስ ህይወትን ዘርቶ ዝልፍልፍ ነው ፀጉርሽ እንዳሻው ተኝቷል ወገብሽን እንዳላይ ደብቆ ይዞታል ዳሌሽም ተስማምቶ በምቾት ተቀምጧል ሽንጥሽ ለእጄት ያክል ለመያዣ ቀርቷል ጨረቃም አትውጣ ፀሀይም ትጥለቅ ጥርስሽ ላገር በቂ የሚያንፀባርቅ ኮኮቦች በላይሽ ከበው ያወራሉ ውበትሽ ማርኳቸው ዙርያሽን ያያሉ ጌጣጌጥሽን ጣይው ኩሉስ ለምንሽ እንከን ሳይወጣለት ተፈጥሮ ገላሽ መቀነትሽን ፍቺው ምን አንጀት አለሽ እባብ እና ነበር ቀንተው እያዩሽ አይንሽም ቅዱስ ነው ክፋት እንዳያይ ተረከዝሽ እንቡጥ ችሎ አቆመሽ ወይ ጠረንሽ የአበባ ንብን ያሳስታል ውበትሽ ለግላጋ ሰውን ያስገምታል
Writer(s): Samuel Alemu, Dawit Mellesse Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out