유사한 곡
크레딧
실연 아티스트
Michael Belayneh
실연자
작곡 및 작사
Michael Belayneh Hailu
송라이터
프로덕션 및 엔지니어링
Michael Belayneh
프로듀서
가사
ይመጣል ናፍቆቷ ላያስተኛኝ ምሎ
የልቤን መሳነፍ መራቅ ተከትሎ
ደጋግሞ ከአይኔ ላይ ምስሏ ይከሰታል
አብዝቼ ያሰብኩት ሰው እንደሷ የታል
ተናውጣለች ነፍሴ በእንግዳ ማእበል
ግን ሳለየው እንዴት አፈቀርኳት ልበል
በትር እንደቃጣች አልመክት በክንዴ
ለዛ ልብ ታጋይ ልረታ ነው እንዴ
ተፈጥራ እንጂ ይውደድሽ ተብላ
ስሜቴን ምን ለየው ከሌላ ከሌላ
መላመድ አልለው ገና በሳምንቱ
አይኖቿን መናፈቅ ምንድነው ምክንያቱ
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል በቃል ያወደስኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል በአይኔ የናፈኩት
ይመጣል ናፍቆቷ ላያስተኛኝ ምሎ
የልቤን መሳነፍ መራቅ ተከትሎ
ደጋግሞ ከአይኔ ላይ ምስሏ ይከሰታል
አብዝቼ ያሰብኩት ሰው እንደሷ የታል
ጉልበት ሰቷት እንጂ ልቤ እሷን ማለቱ
ምን ያቆነጃታል ታድያ በየለቱ
ልወዳት ካልሆነ ፍቅሯ ሊቆራኘኝ
እሷን ብቻ ሚያሰኝ ምን ነገር አገኘኝ
ናፍቄ አልጠግብ ያቺን አደይ መሳይ
ደስ ይለኛል ደሞ ተገኝታ አይኖቿን ሳይ
ስሰነብት ሌት ቀን ሲቆጠር
ፍቅሯ ክንፍ አርጎኝ መታየቴ አይቀር
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል ሳላውቅ ያመንኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል ሁሌ ያስታወስኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል በቃል ያወደስኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል በአይኔ የናፈኩት
Written by: Michael Belayneh Hailu