가사

አሞራ ወድጄ አሞራ ሆኛለው ነብርን ወደጄ ነብር ሆኜ አውቃለው ድብ አንበሳም ነበርኩ ከጥንት ተዋድጄ ዛሬ ግን አቃተኝ ብርቄን ሰው ወድጄ ሰው መሆን አልቻልኩም ብርቄን ሰው ወድጄ ተው አንተ ሰው ልቤን አደከምከው ተው አንተ ሰው ልቤን አደከምከው ዘንድሮ ይህ መውደድ የጣለብኝ እዳ ሰው እንዴት ይወዳል ሰውን ሳይረዳ ፍቅር አጠናገረኝ እንደ ጠጠር ምች መድሃኒት ፈልጉ 'ምታውቁ ሰዎች ተው(ተው) አንተ ሰው አሞራ ወድጄ አሞራ ሆኛለው ነብርን ወድጄ ነብር ሆኜ አውቃለው ድብ አንበሳም ነበርኩ ከጥንት ተዋድጄ ዛሬ ግን አቃተኝ ብርቄን ሰው ወድጄ ሰው መሆን አልቻልኩም ብርቄን ሰው ወድጄ ተው አንተ ሰው ልቤን አደከምከው ተው አንተ ሰው ልቤን አደከምከው እኔም ግራ ገብቶኝ ግራ አጋባው ሰው ፍታኝ ከዚህ ማሰር ፍታኝ አንተ ሰው እንዲህ ከሆነማ የፍቅር ነገር ከሃውልት ከድንጋይ ከእንጨት ልቆጠር ተው(ተው) አንተ ሰው ተው(ተው) አንተ ሰው ንገረኝ አንተ ልጅ ዝም አትበለኝ ምነው ጉንፋን እኮ አይደለም የያዘኝ ፍቅር ነው ቀልቤ ተበታትኖ ማሰብ ተስኖኛል ሰው አርገኝ አንተ ሰው ሰው መሆን አቅቶኛል ተው(ተው) አንተ ሰው ተው ተው ተው አንተ ሰው
Writer(s): Ejigayehu Shibabaw Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out