Tekst Utworu

ጊዜው ይርዘም እንጂ መች እረሳሀለው በሆነው ባልሆነው እናፍቅሀለው በል ይግረምህ እና ዛሬም ወድሀለው አንጀቴን አስሬ ይኸው እኖራለው ርቄ ሄጃለው ሁሉን ትቼ ትዝታን በልቤ አስቀርቼ ምነው የምቀጣ የምቸገር ከቶ ምን ይሆን ያንተ ሚስጥር ተማምነው ተዋደው አብረው የኖሩት ሲለዩት ይፋጃል እንደ እግር እሳት እንደ እግር እሳት በልቤ ወድጄ በአፌ የማቀብጥህ ትቼ የማልተውህ እኔው ነኝ ወዳጅህ አይቻልም እና የአንዳንድ ሰው ናፍቆት መውደድን በወጉ ፍቅር ያስተማሩት ርቄ ሄጃለው ሁሉን ትቼ ትዝታን በልቤ አስቀርቼ ምነው የምቀጣ የምቸገር ከቶ ምን ይሆን ያንተ ሚስጥር የልቤ ምሰሶ ዘንጉ ተሰበረ የማይመነጠር ምሽግ የነበረ ምሽግ የነበረ በፅኑ ትዝታ በራቀው መንገዴ እስቲ ላሰላስልህ ደግሞ እንደ ልማዴ ይኸው ልቤ ጥሎኝ ተነስቶ ሲሄድ ባንተ መወስወሱን አድርጎ ልማድ አድርጎ ልማድ
Writer(s): Aster Aweke Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out