Lyrics

የቱ ውበት ነው እንዳንቺ የተዋጣለት የቱ አመል ነው እንከን የማይገኝለት ልብን ወስዶ መንፈስን የሚገዛ የሚያሸንፍ ቀን በቀን የሚበዛ ይሄ ሁሉ መባረክና ማማር ከየት ነው ምንጩ ንገሪኝ እስቲ የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር ውበት ቁንጅናሽን በቃል ለማስረዳት የቋንቋ እውቀት ያለው ያስፈልጋል ረዳት ቃላት ላይ ፊደል ላይ ስልጣን የሌለው ሰው አይችልም አይችልም ውበትሽን ሊገልጸው ውበት ቁንጅናሽን በቃል ለማስረዳት የቋንቋ እውቀት ያለው ያስፈልጋል ረዳት ቃላት ላይ ፊደል ላይ ስልጣን የሌለው ሰው አይችልም አይችልም ውበትሽን ሊገልጸው ቆንጆ ናት መቼ ይገልጽሻል ቁም ነገር አስቀርቶብሻል ጥሩ ናት መቼ ይገልጽሻል ውበትን ይደብቅብሻል የኔ ማር ቃል እስካገኝ ድረስ የኔ ማር የሚሄድ ካንቺ ጋር የኔ ማር ዝም ብዬ ልውደድሽ የኔ ማር እያልኩሽ የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የቱ ውበት ነው እንዳንቺ የተዋጣለት የቱ አመል ነው እንከን የማይገኝለት ልብን ወስዶ መንፈስን የሚገዛ የሚያሸንፍ ቀን በቀን የሚበዛ ይሄ ሁሉ መባረክ እና ማማር ከየት ነው ምንጩ ንገሪኝ እስቲ የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የማማርሽ ዝና ተዳርሶልሽ ባለም ስታምር ስታምር የማይልሽ የለም የውበት መለኪያው ሳይለካ ኖሮ ውበት ማለት አንቺ ሆነሻል ዘንድሮ የማማርሽ ዝና ተዳርሶልሽ ባለም ስታምር ስታምር የማይልሽ የለም የውበት መለኪያው ራሱ ተለክቶ መለካቱን ትቷል ባንቺ ተተክቶ ቆንጆ ናት መቼ ይገልጽሻል ቁም ነገር አስቀርቶብሻል ጥሩ ናት መቼ ይገልጽሻል ውበትን ይደብቅብሻል የኔ ማር ቃል እስካገኝ ድረስ የኔ ማር የሚሄድ ካንቺ ጋር የኔ ማር ዝም ብዬ ልውደድሽ የኔ ማር እያልኩሽ የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር የኔ ማር
Writer(s): Abdu Kahssay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out