Lyrics

ይገርማል ካዩት ላንድ አፍታ ይጮሀል ለካ ዝምታ ትግስቱ የበዛ አይደለም የዋዛ ይልቅ ከሚያወራው ዝም ያለውን ፍራው ይገርማል ካዩት ላንድ አፍታ ይጮሀል ለካ ዝምታ ትግስቱ የበዛ አይደለም የዋዛ ይልቅ ከሚያወራው ዝም ያለውን ፍራው እናት ዥንጉርጉር እውነትም ነው ሆዷ አየሁ ሁለት ሰው ክፉ ደግ ወልዳ አቤል ተከሶ ሰው ተኳርፎ ከይሉኝታ ቃየል ነገሠ በምድሪቷ በልጦበት ጥቅም ለዲናር ቆሞ ወዳጅ ወዳጁን ይሸጣል ስሞ አውቆ ነው ያ ሰው አንገት መድፋቱ ዝም ያለው ጠልቶ እሪ በከንቱ በልጦበት ጥቅም ለዲናር ቆሞ ወዳጅ ወዳጁን ይሸጣል ስሞ አውቆ ነው ያ ሰው አንገት መድፋቱ ዝም ያለው ጠልቶ እሪ በከንቱ ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም ይገርማል ካዩት ላንድ አፍታ ይጮሀል ለካ ዝምታ ትግስቱ የበዛ አይደለም የዋዛ ይልቅ ከሚያወራው ዝም ያለውን ፍራው ይገርማል ካዩት ላንድ አፍታ ይጮሀል ለካ ዝምታ ትግስቱ የበዛ አይደለም የዋዛ ይልቅ ከሚያወራው ዝም ያለውን ፍራው ቃል እየበላ ለማደር የዛሬን ጎርሶ አለ የሚኖር ከአራዊት አንሶ ይከበር እንጂ ጨዋ ሆኖ ድል አድራጊ እውነት ተናግሮ ባመሸው አንጊ ብልህ አይጥልም ቀድሞ በወሬ ፍራ ዝምታን ልብ በል ዛሬ አክብረው ስማ ያን ሰው ይልቅ ስለመረጠ ዝምታን ወርቅ ብልህ አይጥልም ቀድሞ በወሬ ፍራ ዝምታን ልብ በል ዛሬ አክብረው ስማ ያን ሰው ይልቅ ስለመረጠ ዝምታን ወርቅ ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም ዝም አይነቅዝም አይነቅዝም
Writer(s): Solomon Ambaw Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out