Lyrics

ሰላምሽን አጥተሻል መሰለኝ እኔስ ምን ላድርግሽ ቸገረኝ አታቀርቅሪ ቀን ያልፋል ሃሳብ ለሌላም ይተርፋል እባክሽ ቀና በይ እኅቴ ሲከፋሽ ይባባል አንጀቴ ምን ያስፈልጋል ትካዜዉ ሁሉም ይሆናል በጊዜዉ በትካዜ የተዋጡ ዓይኖችሽ ያባባሉ ውብ ጥርሶችሽ ሳቅ የመረራቸዉ ይመስላሉ አቤት አቤት ሁኔታሽ ይነካል ስሜት ሁኔታሽ አቤት አቤት ኀዘንሽ ይነካል ስሜት ኀዘንሽ ቀና ብለሽ እርዳኝ እንደማለት ችግርሽን አቀርቅረሽ ምነዉ ባታስከፊዉ ፈጣሪሽን ለበጎ ነዉ ሁሉም ነገር ለበጎ ነዉ ሚሆነዉ ለበጎ ነዉ ሁሉም ነገር ለበጎ ነዉ ሚሆነዉ ከፍቶሽማ አንገትሽን ደፍተሽማ አዝነሽማ እኔ አልይሽ ጨንቆሽማ ጌታ ያዉቃል ቀና በይ ከእንግዲማ ሰላምሽን አጥተሻል መሰለኝ እኔስ ምን ላድርግልሽ ቸገረኝ አታቀርቅሪ ቀን ያልፋል ሃሳብ ለሌላም ይተርፋል እባክሽ ቀና በይ እኅቴ ሲከፋሽ ይባባል አንጀቴ ምን ያስፈልጋል ትካዜዉ ሁሉም ይሆናል በጊዜዉ ምኞትሽን ባንቺ ፈቃድ ስበሽ ላትጨብጪዉ ይጎዳሻል እንደዉ ለትካዜ ፊት አትስጪዉ አቤት አቤት ሁኔታሽ ይነካል ስሜት ሁኔታሽ አቤት አቤት ኀዘንሽ ይነካል ስሜት ኀዘንሽ ቢለያዪም መከራና ደስታ በየመልኩ ሁሉም ነገር ከወሰን አያልፍም ያው ከልኩ ለበጎ ነዉ ሁሉም ነገር ለበጎ ነዉ ሚሆነዉ ለበጎ ነዉ ሁሉም ነገር ለበጎ ነዉ ሚሆነዉ አዝነሽማ ፍዝዝ ትክዝ ብለሽማ አቀርቅረሽ አንገትሽን ደፍተሽማ ከፍቶሽማ እኔ አልይሽ ከእንግዲማ ጌታ እስካለ ቀና በይ ከእንግዲማ አዝነሽማ እኔ አልይሽ ጨንቆሽማ ከእንግዲማ ቀና በይ ከእንግዲማ
Writer(s): Danial Tekle Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out