Lyrics

ባልኩሽ እምላለው በስሙ እኔን ይዤ እወድሻለሁ ስልሽ እውነት እውነት ከልቤ አልዋሽሽም ምንም የሰው ስም ጠርቼ እወድሻለሁ ስልሽ እውነት እውነት ከልቤ ለምኔ ስል ልዋሽ ምን አገኝ ብዬ አንቺን ዋሽቼ አትጠራጠሪ ምንም አልዋሽም የልቤን እኔ እወድሻለሁ ስልሽ እውነት እውነት ከልቤ በብሩህ ሰማይ ስር ማለዳ እንደ ወጣች ፀሐይ ፈንጥቃ ኩልል እንዳለ የምንጭ ውሃ ፍቅርሽ አይጠገብ አይበቃ አይኖርም የሚያሸሸው ልቤን ያንቺን ፍቅር ከቶ የሚያከስመው ልንገርሽ ሁሉም የሚያስታውሰኝ የያዝኩት ወርቅ አልማዝ መሆኑ ነው በቃ አታስቢው ይቅር እምላለሁ የፍቅሬን መጠን በቃል ከምገልፀው በላይ እወድሻለሁ የለም አይኖርም ሌላ ካንቺ ወዲያ ፍቅሬ እምላለሁ እመኚኝ ያልኩሽ እውነት የምር ነው እወድሻለሁ ባልኩሽ እምላለው በስሙ እኔን ይዤ እወድሻለሁ ስልሽ እውነት እውነት ከልቤ አልዋሽሽም ምንም የሰው ስም ጠርቼ እወድሻለሁ ስልሽ እውነት እውነት ከልቤ ለምኔ ስል ልዋሽ ምን አገኝ ብዬ አንቺን ዋሽቼ አትጠራጠሪ ምንም አልዋሽም የልቤን እኔ እወድሻለሁ ስልሽ እውነት እውነት ከልቤ ሰፊ እና ጥልቅ ነው መውደዴ እመኚኝ ከባህር ይልቃል ቢወጡት ቢወርዱት ድካም ነው አትልፊ ማመኑ ይቀላል የሽንገላ አይደለም ከልቤ ያደረው እውነት እስካሁን ቃላት አይገልፁትም እስካሁን እወደዋለሁ ስልሽ ስሜቱን በቃ አታስቢው ይቅር እምላለሁ የፍቅሬን መጠን በቃል ከምገልፀው በላይ እወድሻለሁ የለም አይኖርም ሌላ ካንቺ ወዲያ ፍቅሬ እምላለሁ እመኚኝ ያልኩሽ እውነት የምር ነው እወድሻለሁ
Writer(s): Samuel Alemu, Hayleyesus Feyssa Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out