Lyrics

ድምሬ በሆንክልኝ ደስታዬ በሞላልኝ ስጦታ በሆንኩለት በእቅፉ በዋልኩለት የትኛዉ ተራራ ሸስጎህ ነበረ ባላመንኩት ቦታ ልቤ ከታሰረ እንባ ሞልቶት አይኔን ከልሎኝ የፊቴን አንተን መሳይ ጉብል ነፈኩት ህይወቴን ዘመን ተመልሶ በእቅፍህ በዋልኩኝ በፍቅርህ ሁዳዴ በአንተዉ በገደፍኩኝ የፍቅር ቡቃያ ጭንጫ ላይ ዘርቼ ስንት ዘመን ገብቶ የአንተን ብጤ አጥቼ የት ነበርክ ልበልህ በከፋዉ ዘመኔ እንኳንስ ገላዬ ሲናፍቅህ አይኔ ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ ድምሬ በሆንክልኝ ደስታዬ በሞላልኝ ስጦታ በሆንኩለት በእቅፉ በዋልኩለት የትኛዉ ተራራ ሸስጎህ ነበረ ባላመንኩት ቦታ ልቤ ከታሰረ እንባ ሞልቶት አይኔን ከልሎኝ የፊቴን አንተን መሳይ ጉብል ነፈኩት ህይወቴን ዘመን ተመልሶ በእቅፍህ በዋልኩኝ በፍቅርህ ሁዳዴ በአንተዉ በገደፍኩኝ አሻግሬ ሳየዉ ዘመኔ ይቆጨኛል ለአንተ አለመዋሉ ያንገበግበኛል በቃ እንግዲህ ሳልሆነዉ ክፉ ደግ አይቼ አንተን ሰፈርኩበት ከሌሎች ለይቼ ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ የማይሰማ ምጣድ ሳስስ የፈሰሰ ዉሃ ሳፍስ ፈጀሁት ዘመኔን አንድጄ የማይበስል እንጐቻ ጥጄ የማይሰማ ምጣድ ሳስስ የፈሰሰ ዉሃ ሳፍስ ፈጀሁት ዘመኔን አንድጄ የማይበስል እንጐቻ ጥጄ ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
Writer(s): Elias Woldemariam, Temesgen Afework Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out