album cover
Amalay
1,601
Hip-Hop/Rap
Amalay was released on February 15, 2021 by Atgebam Alugn as a part of the album Atgebam Alugn
album cover
Release DateFebruary 15, 2021
LabelAtgebam Alugn
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM89

Credits

PERFORMING ARTISTS
Lij Michael
Lij Michael
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Lij Michael
Lij Michael
Songwriter

Lyrics

ተውባ
ተውባ ተውባ
እንደ አደይ አበባ
(አማላይ)
(አማላይ) አንቺ አማላይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
የመውደድ የፍቅር ገዳይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
የመውደድ የፍቅር ገዳይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
አምራ ደምቃ ተውባ
ትታያለች ከሩቅ እንደ አደይ አበባ
ፍቅር ደስታ ጨዋታ
ልብን ይማርካል የእሷማ ፈገግታ
ጥርሷ ጉራማይሌ (ጥርሷ ጉራማይሌ)
ፀጉሯ የጤፍ ነዶ (ፀጉሯ የጤፍ ነዶ)
ጎንበስ ቀና ይላል (ጎንበስ ቀና ይላል)
ሀገር እሷን ወዶ (ሀገር እሷን ወዶ)
ባለነጠላ ናት ደምባላ ጥማዶ
ፍቅሯ ስንቱን ጣለው ደርቦ ደርቦ
የቀይ ዳማ ቆንጆ ቢሉሽም ጠይም
ሲስሟት የምጥም የሰንደል ቀለም
አማላይ ነሽ በቃ ስምም ወቶልሻል
ከዚ በላይ ሌላ ማንስ ይሰጥሻል
ይዘናፈል ተይው ወድቆ ከትከሻሽ
ፀጉርሽ ምን ባጠፋ ይታሰራል በሻሽ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
የመውደድ የፍቅር ገዳይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
የመውደድ የፍቅር ገዳይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
ሞገስ አመል ፀባይ
ይወጣል ይታያል ለይቶ በእሷ ላይ
ክብር መውደድ ቅንነት
ሁሉን የሞላ ነው የእሷማ ማንነት
ሁሉም እሷን ይላል (ሁሉም እሷን ይላል)
ሰፈር ሀገር ሁሉ (ሰፈር ሀገር ሁሉ)
ትምጣ ትምጣ ባይ ነው (ትምጣ ትምጣ ባይ ነው)
ነገረኛ ሁሉ (ነገረኛ ሁሉ)
አመለ ሸጋ ልጅ ወርቀ ሰለበት
ብለው የሚጠሩሽ የቤቱ እመቤት
የሴት ባለሙያ የውበት መደቡ
ሀገር እጅ የነሳት እቺ ልጅ ተዋቡ
አንቺ ምን ታረጊ ጉዱ ከቤትሽ
ማማርሽ ሳይበቃ እየማሉብሽ
እስኪ ሳሚኝና ሀገሬው ጉድ ይበል
እኔ ወጣ ብዬ አገኘኋት ልበል
(አማላይ) አንቺ አማላይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
የመውደድ የፍቅር ገዳይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
የመውደድ የፍቅር ገዳይ
(አማላይ) አንቺ አማላይ
Written by: Lij Michael
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...