album cover
Tesasatn
131
Hip-Hop/Rap
Tesasatn was released on May 27, 2022 by Birrz Studio as a part of the album Lewt
album cover
AlbumLewt
Release DateMay 27, 2022
LabelBirrz Studio
LanguageEnglish
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM89

Credits

COMPOSITION & LYRICS
Kidus H Worku
Kidus H Worku
Songwriter
SAMUEL TEFERI
SAMUEL TEFERI
Songwriter

Lyrics

ዛሬ የተከሉት ፍሬ ነገ እንደሚያብበው
የሰጠውን ነው ሰው የእጁን ነው የሚያገኘው
አከብራለው ምርጫዋ ነው እሷ የፈቀደቺው
ግን ተከትላ ነው ሄዋን መንገድ የሳተችው
የጣልሽው ወርቅ ነው ፍቅር የሰው ቤት እያየሽ
መኞት አሸነፈሽ ጥቅም ከጎረቤት አድረሽ
ማንነት ቀይረሽ ቅዠት የሰው ስታደምቂ
ህልምሽን ገድለሽው ወድቀሻል ስትነቂ
ግን አይቆይም ለዘላለም ዉቡ ወጣትነት
ሳንገነባ ነጋችንን ትሄዳለች ድንገት
ለማያይሽ ዞሮ ነገ ልሙትልሽ ያለሽ
የበላሽው ገንዘብ ቁማር ህይወት አስከፈለሽ
ሳታውቂበት መርጠሽ ይሆን አሳሳች ጓደኛ
ትቆጥራለች እየጣለች አንቺን እያለች ስንተኛ
የገባሽው ከክፉ አለም ዉሸት ከሚያዞራት
ደስታ የለ ጭንቀት ብቻ ሀጣን ከሚመሯት
ለብልጭልጭ ለቁስ ሁሉንም እያወቅሽ
ክብርሽን ገለሽው ወዳጅሽን ገፍተሸ
ንግድ ስታደርጊያት ፍቅርን ክብሯን ንቀሽ
ላንቺ የነሩትን ጥለሽ ሲጠፋ ህሊናሽ
እሱ ጋር ተሳሳትሽ አዎ
እሱ ጋር ተሳሳትሽ አኸ
እሱ ጋር ተሳሳትሽ አዎ
እሱ ጋር ተሳሳትሽ አኸ
እሱ ጋር ተሳሳትሽ
እሱ ጋር ተሳሳትሽ
እሱ ጋር ተሳሳትሽ
እሱ ጋር ተሳሳትሽ
ነፍሴን ስጠይቀው አለኝ ቃልህ ይሁን አውነት
አልቅሶ ይውጣለት ቀለም ብዕሩን ፃፍበት
አትሸነፍ በዚች አለም ዝም አትበል ስህተት
አቅምህ ይሄ ነው ስራ ሀቅ ጥበብ መስጠት
ያከበርነው የሚመስለው እኛ ያልነው ትልቁ
የነበረው የደረሰው ዝም ያለው ሲሰርቁ
የሙስና አለቃ ነበረው ቤተሰብ ቅሉ
እየጣለ ፍቅር እምነት እነሱ እየሰጡ
ክብር የለው ለምትወደው ለዛች ውድ ሚስቱ
ልጆቿን እያለች ሆና ስንቱ ድካሟ ዋለ ከንቱ
አሁንማ አይመለስ ሄዷል እሱ እርቆ
በውሸት አዙሪት ገብቶ ለስሜቱ ወድቆ
ህልሟን የገደልከው ያቺ ወጣት
በደካማ ጎኗ ከጉዞ ያቆምካት
በስሜት ተመርተህ በገንዘብ የጣልካት
ልክ እንደ አንተው ሚጣ የአንድ አባት ልጅ ናት
መልካሙንም መጥፎንም ምርጫህ ነው የሚያደርገው
የነገም አበባ አሜኬላው ፍሬው በእጅህ ነው ያለው
ዛሬ መርጠህ ፍቅር ወደ ቤትህ ካልዞርክ
ለራስህ ምስኪን ልጅ ጥሩ አባት ካልሆንክ
እሱ ጋር ተሳሳትክ አዎ
እሱ ጋር ተሳሳትክ አኸ
እሱ ጋር ተሳሳትክ አዎ
እሱ ጋር ተሳሳትክ አኸ
እሱ ጋር ተሳሳትክ
እሱ ጋር ተሳሳትክ
እሱ ጋር ተሳሳትክ
እሱ ጋር ተሳሳትክ
ጊዜ ሲያልፍ ፀሎቴ ነው እኔ እንዳልቀየር
እያወቅኩኝ ተሳስቼ በነብር እንዳልቀር
እፈራለው ድንገት የሰው ልብ እንዳልሰብር
ይጨነቃል ልቤ ሰው ማውራቱ ላይቀር
ያስተምራል ብዙ ነገር በመከራ ማለፍ
ይረሳል በጊዜ ህይወት ግን ስትል ከፍ
የበረረም ያርፋል ማንም አይቀር ከጫፍ
የወጣም የወርዳል በአዲስ ህይወት ምዕራፍ
እንደ ትላንት አደለንም እኛ ሁላችንም
አሳልፈን አይተነወል ወድቀን ተነስተንም
አጥፍተናል ትላንት ላይ ሳናውቅ አውቀንም
ለመመለስ ለይቅርታ ዛሬም አያረፍድም
ግን ለራሴ ብቻ እያልኩ ያመኑኝን ክጄ
የችግሬን የክፉ ቀን ወዳጆቼን ትቼ
ጊዜ ሲያስረሳኝ መነሻዬን ክፋትን መርጬ
ማንነቴን ከጣልኩ ፍቅርን ዘንግቼ
ሰው ላረጉኝ ላበረቱኝ ልቤ ካጣ ቦታ
ካስቀደምኩኝ ገንዘብ የእውነት ጥበብ ወድቃ
ሌላውን አጠፋ ብዬ እኔ እየተሳሳትኩ
ንፁ አድርጌ እራሴን ሁሉን አቃለው ከልኩ
እሱ ጋር ተሳሳትኩ አዎ
እሱ ጋር ተሳሳትኩ አኸ
እሱ ጋር ተሳሳትኩ አዎ
እሱ ጋር ተሳሳትኩ አኸ
እሱ ጋር ተሳሳትኩ
እሱ ጋር ተሳሳትኩኝ
እሱ ጋር ተሳሳትኩ
እሱ ጋር ተሳሳትኩኝ
እሱ ጋር ተሳሳትኩ
እሱ ጋር ተሳሳትኩኝ
እሱ ጋር ተሳሳትኩ
እሱ ጋር ተሳሳትኩኝ
Written by: Kidus H Worku, SAMUEL TEFERI
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...