album cover
Lefaw
album cover
Lefaw was released on February 7, 2023 by The Milo Mix as a part of the album Vol ፫
AlbumVol ፫
February 7, 2023
LabelThe Milo Mix
BPM87
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy

Music Video

Music Video

Lyrics

አዎ ፍቅር ስንት አይቻለው
እመኚኝ ብዙም አውቃለው
ወዶም ተወዶም እንዲ አልገጠመውም
ልቤ እውነቱን ቁርጡን አውቆልኝ
ቢቆርጠኝ ቢፀናልኝ
የልብሽን ሀሳብ አንቺው ንገሪኝ
ይህን ምክንያት ያን ምክንያት እያረግሽው ሰበብሽ
በቃ አትሆነኝም ብዬ ትቼም እንዳልተውሽ
ወይ እንዲ ነው ብለሽ ግልጡን አልነገርሽኝ
አለው ተስፋ ብቻ አዝዬ የኔ እንድትሆኝ ብዬ
ለፋው ስንት ለፋው ስንት ለፋው
ከልብሽ ደጃፍ እየተገፋው
ለፋው ስንት ለፋው ስንት ለፋው
ከልብሽ ደጃፍ እየተገፋው
በይ እመኚኝ ያንቺ ይለያል
እንዳልፈርድም ቸግሮኛል
ከላይ ከላይ የሚታየው
ሳቅሽ ተስፋን ነው የሚያበስረው
የቸገረኝ ምክንያት ያጣሁለት
ከፈገግታሽ ጀርባ ያለው ያንቺ እውነት
የቱ ጋር እንደው ልወቀው እና
ልለይሽ ጨክኜ ወይ ልፅና
ይህን ምክንያት ያን ምክንያት እያረግሽው ሰበብሽ
በቃ አትሆነኝም ብዬ ትቼም እንዳልተውሽ
ወይ እንዲ ነው ብለሽ ምክንያት አልነገርሽኝ
አለው ተስፋ ብቻ አዝዬ የኔ እንድትሆኝ ብዬ
ለፋው ስንት ለፋው ስንት ለፋው
ከልብሽ ደጃፍ እየተገፋው
ለፋው ስንት ለፋው ስንት ለፋው
ከልብሽ ደጃፍ እየተገፋው
ግልጡን ንገሪኝ ልወቀው
ካንደብትሽ ካንቺው ልስማው
ከልብሽ ካለ ሌላ ሰው
ችዬ ምኞቴን ላስታግሰው
ግልጡን ንገሪኝ ልወቀው
ካንደብትሽ ካንቺው ልስማው
ከልብሽ ካለ ሌላ ሰው
ችዬ ምኞቴን ላስታግሰው
ታግሶ ለኖረ ጠብቆ
መኖር ይሻለዋል ቁርጡን አውቆ
የኔ ብትሆኚ ነው ምኞቴ
በክንቱ እንዳይቀር ልፋቴ
ታግሶ ለኖረ ጠብቆ
መኖር ይሻለዋል ቁርጡን አውቆ
የኔ ብትሆኚ ነው ምኞቴ
በክንቱ እንዳይቀር ልፋቴ
በከንቱ እንዳይቀር ልፋቴ
በከንቱ እንዳይቀር
Written by: Natnael Ayalew Yimer
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...