Lyrics

በለሷን ፍሬዋን የጠበቀ ይበላል ትግስቱ ያላለቀ ጌታውን የጠበቀ ሰው ስፍሪዬን አለቅም ያለው እሱ ሰው ከበረ አሄ ጌታን ያከበረ እሱ ሰው ከበረ አሄ ጌታን ያከበረ ስሞዖን ትጉህ ሰው ፃድቅ ሰው ነበረ አያለው ቅዱሱን እያለ የኖረ ሲጠብቅ ቆይቶ ህፃኑን ሲያየው እጆቹን አንስቶ እንደዚህ አለው ለህዝቦች ሁሉ መድኃኒት መድኃኒት የሆነውን እሱን ስላየሁት ስላየሁት መኖር አልሻም ውሰደኝ በቃ ውሰደኝ በቃ በፅድቅ የኖርኩት እሱን ጥበቃ ጌታን ጥበቃ ለኔ ስኬት ለኔ ስኬት ለኔ ስኬት ልጁን ማየት ለኔ ከፍታ ለኔ ከፍታ ለኔ ከፍታ ፊትህ ነው ጌታ ያርስ የለ ወይ በበጋ ልቡን ጥሎ ገበሬው አምኖ ይዘንባል ብሎ በደረቅ መሬት አምኖ ያረሰ በክረምት እርሻው እረሰረሰ እኔው እጠብቅሃለው መውደዴን በዚ አሳይሃለው አንድ ቀን ዓለም እያየህ ልትወስደኝ ትመጣልኛለህ እስክትመጣ እስክትመለስ እጠብቅሃለው ውዴ ኢየሱስ ጠነከረብኝ ፍቅርህ በረታ በቶሎ ናልኝ የህይወቴ ጌታ በለሷን ፍሬዋን የጠበቀ ይበላል ትግስቱ ያላለቀ ጌታውን የጠበቀ ሰው ስፍሪዬን አለቅም ያለው እሱ ሰው ከበረ አሄ ጌታን ያከበረ እሱ ሰው ከበረ አሄ ጌታን ያከበረ ፍጻሜው ክብር ነው አንተን መጠበቄ መብራቴን አብርቼ ወገቤን ታጥቄ እጠብቅሃለው እስክትመለስ ሙሽራው አዳኜ ጌታዬ ኢየሱስ ፊትህን እንዳይ ተርቤ የለ ወይ እርቦኝ የለ ወይ ለጥቂቶች መዳን ብትዘገይ ብትዘገይ ጨመረብኝ ፍቅርህ በየዕለቱ በየዕለቱ ተናፍቀሃል ኢየሱስ የናዝሬቱ የናዝሬቱ እስክትመጣ እስክትመለስ እጠብቅሃለው ውዴ ኢየሱስ ጠነከረብኝ ፍቅርህ በረታ በቶሎ ናልኝ የህይወቴ ጌታ
Writer(s): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out