album cover
Degesen
album cover
Degesen was released on February 9, 2024 by ela records as a part of the album Enzira
AlbumEnzira
ReleasedFebruary 9, 2024
Labelela records
BPM115
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy

Music Video

Music Video

Lyrics

ደግሰን ደግሰን ቀኑን ተገባብዘን
እንችለዋለን ወይ ሲመሽ ጦር ተማዘን
መልሶ መልሶ እንደሞኝ ለቅሶ
ተይ አለቅም ማለት አንድ ነገር ይዞ
ኧረ የምን ችክ ነው ችክ አይወድም ፍቅር
ባይሆን ለቀቅ አድርጊው ላላ ሲል ነው የሚያምር
ኧረ የምን ችክ ነው ችክ ያለበትማ
እንኳን ከሚወደው ጋር ከራሱ አይስማማ
እየረፋፈደ በሚመጣ ኩርፊያሽ
አንቺ ለቀናሽው እኔ አጣሁኝ ትንፋሽ
ለዋዜማው እንጂ ሽር ጉድ የሚባል
ማግስቱ ረፍት ነው ፍቅርና አመትባል
አለመደማመጥ ወይ አለመግባባት
ይረሳል ከመሸ ያወራነው ጠዋት
እንኳን ለራሴ ለቤቴ
ለሰው ይዘፍናል አንገቴ
ይላል ሲተርት የሀገር ሰው
ሲከፋው ሆዱን ሲብሰው
እንኳን ለራሴ ለቤቴ
ለሰው ይተርፋል እምነቴ
በአጉል ደጋግመሽ ነክተሽኝ
እልሄን አታስጨርሺኝ
ነካክተው ነካክተው የተኛውን በሬ
አደረጉት አውሬ
ይባል አይደለም ወይ ልብ ያመረረ ቀን
እንዳያራርቀን
ነካክተሽ ነካክተሽ ተይ አታድርጊኝ ኋላ
ቤቴን እንድጠላ
እንዲያ እንዲያ እያለ ልብ ያመረረ ቀን
እንዳያራርቀን
ደግሰን ደግሰን ቀኑን ተገባብዘን
እንችለዋለን ወይ ሲመሽ ጦር ተማዘን
መልሶ መልሶ እንደሞኝ ለቅሶ
ተይ አለቅም ማለት አንድ ነገር ይዞ
ኧረ የምን ችክ ነው ችክ አይወድም ፍቅር
ባይሆን ለቀቅ አድርጊው ላላ ሲል ነው የሚያምር
ኧረ የምን ችክ ነው ችክ ያለበትማ
እንኳን ከሚወደው ጋር ከራሱ አይስማማ
ያን ጊዜ እንደነበር ስልሽ እመቤቴ
ዛሬም አልቀነሰም ሞገስሽ ከፊቴ
ታድያ ለምንድነው እስኪ ልጠይቅሽ
ኮሽ ባለው ሁሉ የሚያስደነግጥሽ
እያደር ውስጥ ውስጡን ሲጨስ እንደአቧራው
ልብሽን ከልክይው ልቤን እንዳይመራው
እንኳን ለራሴ ለቤቴ
ለሰው ይዘፍናል አንገቴ
ይላል ሲተርት የሀገር ሰው
ሲከፋው ሆዱን ሲብሰው
እንኳን ለራሴ ለቤቴ
ለሰው ይተርፋል እምነቴ
በአጉል ደጋግመሽ ነክተሽኝ
እልሄን አታስጨርሺኝ
ነካክተው ነካክተው የተኛውን በሬ
አደረጉት አውሬ
ይባል አይደለም ወይ ልብ ያመረረ ቀን
እንዳያራርቀን
ነካክተሽ ነካክተሽ ተይ አታድርጊኝ ኋላ
ቤቴን እንድጠላ
እንዲያ እንዲያ እያለ ልብ ያመረረ ቀን
እንዳያራርቀን
Written by: Biniamir Ahemed, Natnael Girmachew
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...