album cover
Bitay
3
Worldbeat
Bitay was released on December 12, 2025 by ela records as a part of the album Merhaba
album cover
AlbumMerhaba
Release DateDecember 12, 2025
Labelela records
Melodicness
Acousticness
Valence
Danceability
Energy
BPM120

Music Video

Music Video

Lyrics

በቃ ይሁን ከወሰነች ምን ይደረግ
ልቡ ርቆ የሄደ ሰው አይቆም በሕግ
ብልም ይሄን ሁሉ ብልም
ስትሄጅ አንዱም ጎኔ የለም (+2
መች መሰለኝ እና ውስጤ እንዲህ ሚጎዳ
መሄድሽ አይለመድ እያደር እንግዳ
ቀኑም የግድ ያልፋል ምሽት የለኝ ጤና
ሰው ቤቱ ሲያርፍ ነው ሚያሠኘኝ ጎዳና
ብታይ ያላንቺ እኔ ብታይ
ብታይ ያላንቺ እኔ ብታይ
እኔ አልሆነልኝም ያላንቺ የእኔ ሲሳይ
ህይወት አልሆነኝም ሁለም ሆነ ስቃይ
ብታይ ያላንቺ እኔ ብታይ
አዝማች
በቃ ይሁን ከወሰነች ምን ይደረግ
ልቡ ርቆ የሄደ ሰው አይቆም በሕግ
ብልም ይሄን ሁሉ ብልም
ስትሄጅ አንዱም ጎኔ የለም (+2
ሳቄማ ባዳ ነው አንቺን ብሎ ጓዴ
ተከትሎሽ ሄዷል የለም ከመንገዴ
የክፋ ቀን ደራሽ እምባ ነው ዘመዴ
ናፍቆት ሲያቃጥለኝ ሚፈሠው ከሆዴ
ብታይ ያላንቺ እኔ ብታይ
ብታይ ያላንቺ እኔ ብታይ
እኔ አልሆነልኝም ያላንቺ የእኔ ሲሳይ
ህይወት አልሆነኝም ሁለም ሆነ ስቃይ
ብታይ ያላንቺ እኔ ብታይ
Written by: Nur Akmel
instagramSharePathic_arrow_out􀆄 copy􀐅􀋲

Loading...