Music Video

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Mikaya Behailu
Mikaya Behailu
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Mikaya Behailu
Mikaya Behailu
Songwriter
Elias Woldemariam
Elias Woldemariam
Songwriter

Lyrics

ህህህይ ሰበቡ ብዙ ነው እንዳፈር ለሳሱለትማ ነገር ባላየሁህ ባልወደድኩህ ምን ነበር ህህህይ ምቀኛው ብዙ ነው እንዳፈር ለሳሱለትማ ነገር ባላየሁህ ባልወደድኩህ ምን ነበር እናቴን ተውኩኝ (እናቴን ተውኩኝ) አባቴን ተውኩኝ (አባቴን ተውኩኝ) ፍቅርህን ብዬ (ፍቅርህን ብዬ) ያለኝን ጣልኩኝ (ያለኝን ጣልኩኝ) ላንተ ስል እራሴን ከፈልኩኝ ያለኝን ንብረቴን በተንኩኝ ላንተ ስል እውቀቴንም ናቅኩኝ ክብሬንም ማዕረጌንም ተውኩኝ ላንተ ስል ኑሮዬን መርሳቴ ለፍቅርህ መጥቆሬ መክሳቴ ላንተ ስል ፍፁም አይቆጨኝም አንድም ቀን አይታሰበኝም ህህህይ ሰበቡ ብዙ ነው እንዳፈር ለሳሱለትማ ነገር ባላየሁህ ባልወደድኩህ ምን ነበር ህህህይ ምቀኛው ብዙ ነው እንዳፈር ለሳሱለትማ ነገር ባላየሁህ ባልወደድኩህ ምን ነበር ባላየኸኝ (ባላየኸኝ) ባልወደድከኝ (ባልወደድከኝ) ምነው ያቺን ቀን (ምነው ያቺን ቀን) ባልቀረብከኝ (ባልቀረብከኝ) ላንተ ስል ፍቅርህ ሳይጎድልብኝ አንድም ቀን ሳይቀነስብኝ ላንተ ስል ጤናዬን ጎዳሁኝ ገላዬን በስጋት ጨረስኩኝ ላንተ ስል ሃሳብ ሲያንገላታህ ድንጋይ እንቅፋት ሲመታህ ላንተ ስል እኔስ የሚመስለኝ ስብርብር እንክትክት ያልክብኝ ላንተ ስል ሲያቀብጠኝ ወድጄ (እናቴን ተውኩኝ) ሰስቼህ እንደ ስለት ልጄ (አባቴን ተውኩኝ) ላንተ ስል ሌሊት እና ቀን ቀን (ፍቅርህን ብዬ) ክፉህን አያለሁ ሰቀቀን (ያለኝን ጣልኩኝ) ላንተ ስል ሆዴም ከሚባባ (ባላየኸኝ) መጥኜ እንዲያው በደርባባ (ባልወደድከኝ) ላንተ ስል ወድጄህ በሆነ ጥንቱንም ልቤም ባልባከነ ላንተ ስል ሲያቀብጠኝ ወድጄ (እናቴን ተውኩኝ) ሰስቼህ እንደ ስለት ልጄ (አባቴን ተውኩኝ) ላንተ ስል ሌሊት እና ቀን ቀን (ፍቅርህን ብዬ) ክፉህን አያለሁ ሰቀቀን (ያለኝን ጣልኩኝ) ላንተ ስል ሆዴም ከሚባባ (ባላየኸኝ) መጥኜ እንዲያው በደርባባ (ባልወደድከኝ) ላንተ ስል ወድጄህ በሆነ (ምነው ያቺን ቀን) ጥንቱንም ልቤም ባልባከነ (ባልቀረብከኝ)
Writer(s): Elias Woldemariam, Mikaya Behailu Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out